ፒክ ፎርድ በመርሲሳይዱ ክለብ ለስድስት ተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት የፈረመው በቅርቡ ቢሆንም ቀያይ ሰይጣኖቹ የግብ ጠባቂዎች ሪከርድ ዋጋን በመክፈል ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ አድርገዋል ።
☀ሪያል ማድሪድ ባልተጠበቀ መልኩ አሮን ራምሴን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጥረት ሊያደርግ እንደሚችል Mirror አስነብቧል ።
የራምሴ ኮንትራት በአርሰናል ቤት የሚያበቃው ክረምት ላይ በመሆኑ እና አዳስ ውል ለመፈረም በክለቡም ሆነ በሱ በኩል መግባባት ስለሌለ በቦስማን ህግ መሰረት ወደ ፈለገበት ክለብ ያለ ዝውውር ሂሳብ መጓዝ ይችላል ።
የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ እና የጣሊያኑ ጁቬንትስም የዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ፈላጊዎች ናቸው ።
☀ፉልሀም የሊቨርፑሉን ተከላካይ ናትናኤል ክላይን በጥር ወር የዝውውር መስኮት በውሰት ለማዘዋወር ጥረት የጀመረ ሲሆን የለንደኑ ክለብ አዲሱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒዬሪም ይህ ዝውውር ይሳካል ብለው ተስፋ እንዳደረጉ Sun አስነብቧል ።
ክላይን በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች ለሊቨርፑል አንድ ጨዋታ ብቻ ያደረገ ሲሆን ዠርደን ክሎፕ በቦታው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ወይንም ጆ ጎሜዝን ነው የሚጠቀሙት።
ራንዬሪ ክለባቸው የሊጉ ግርጌ ላይ መሆኑን ተከትሎ የተከላካይ መስመራቸውን ማጠናከር በእጅጉ ይሻሉ ።ሆኖም በክላይን ጉዳይ ካርዲፍ ሲቲም ፍላጎት አለው።
☀ የሊቨርፑሉን ታዳጊ ቦቢ ዱንካን ለማዘዋወር ባየርን ሙኒክ እየሰራ እንደሆነ Mirror አስነብቧል ።
የ17 አመቱ ተጨዋች የስቴቭን ዤራርድ የስጋ ዘመድ ከማንቸስተር ሲቲ ታዳጊዎች ቡድን የተዘዋወረውም በዘንድሮው አመት ነበር ።
ተጨዋቹ ወደ ቡንደስሊጋው ተጉዞ ከጃደን ሳንቾ እና ሬስ ኔልሰን በኃላ ስኬታማ እንግሊዛዊ ሊሆን ይችል ይሆን ? መልሱን አብረን እንመለከታለን
☀ ጆዜ ሞሪንሆ የናፖሊውን ተከላካይ ኩሊባሊ ለማዘዋወር ክለባቸው €103M አቅርቦ ውድቅ መደረጉን አምነዋል ።ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቸስተር ዪናይትድ በተለይ ዋነኛ ችግሩ የተከላካይ መስመሩ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ ።ክሪስ ስሞሊንግ፤ኤሪክ ቤሊ እና ቪክቶር ሊንደሎፍ መጎዳታቸው ደግሞ ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል ።
በዚህም ምክንያት ቀያይ ሰይጣኖቹ ሴኔጋላዊውን ጠንካራ የኔፕልሱ ክለብ ተጨዋች የማዘዋወር ፍላጎቱ አይሏል ።
☀ ቼልሲ ብራዚላዊውን የፖርቶ ተከላካይ ኤደር ሜሌታኦ ለማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው Dail mail አስነብቧል ።
ሜሌታኦ ከሳኦ ፓውሎ ፖርቶን ከተቀላቀለ ገና ስድስት ወሩ ቢሆንም በፖርቹጋሉ ክለብ እያሳየ ያለው አስደናቂ አቋም ግን በበርካታ የአውሮፓ ጉምቱ ክለቦች አይን ውስጥ ከወዲሁ እንዲገባ አድርጎታል ።
ከቼልሲ በተጨማሪ የ20 አመቱን ተከላካይ ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ማንቸስተር ሲቲ፣ኤቨርተን እና ጁቬንትስ በጥብቅ ይፈልጉታል ።
☀Don ballon እንደዘገበው ከሆነ ሪያል ማድሪድ ሁለት ተጨዋቾችን ከአርጀንቲናው ክለብ ሪቨር ፕሌት ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል ።
ሁለቱ ተጨዋቾች ኤግዙዌል ፓላሲሎስ እና ሁዋን ኩንቴሮ ሲሆን ጋዜጣው እንደዘገበው ከሆነ ይህ ዝውውር ተገባዷል ማለት ይቻላል ።
☀ የአርሰናሉ ኮከብ ሜሱት ኦዚል በቀጣዩ አመት ከመድፈኞቹ ቤት ውጪ ያሉ አማራጮችን ሊያስብ እንደሚችል sun of Sunday አስነብቧል ።ጋዜጣው በእሁድ እትሙ በሰፊው እንዳተተው የጀርመናዊው የጨዋታ ቀማሪ ቀጣይ ማረፊያ የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ሊሆን እንደሚችል ነው ያስነበበው።
☀ኤሲ ሚላን የባርሴሎናውን አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ ለማዘዋወር አርሰናል እና ቼልሲ የሚያደርጉት ፉክክር ውስጥ እጁን አስገብቷል ሲል Sunday Express, via Calciomercato አስነብቧል ።የ24 አመቱ አማካይ በዘንድሮው አመት መልቀቁ አይቀሬ ነው የሚለው ዜና በስፋት በመዘገብ ላይ ይገኛል ።
No comments:
Post a Comment