Saturday, December 1, 2018

ሮናልዶ በጁቬንትስ ለ60 አመት የተያዘን ሪከርድ ተጋራ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጁቬንትስ ቤት አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል 


ፖርቹጋላዊው ኮከብ ቱሪን ከደረሰ ወዲህ በአዲሱ ክለቡ ሪከርዶችን በመሰባበር አጀማመሩን መልካም አድርጓል ።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ፊዮረንቲና ላይ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ ከስልሳ አመት በኃላ በጁቬንትስ ታሪክ ድንቅ አጀማመር ያደረገ ተጨዋች ሆኗል ።

ሮናልዶ በ14 የሴሪያ ጨዋታዎች 10 ግቦችን በማስቆጠር በማድሪድ የሰራውን ገድል ለመድገም እየታተረ ይገኛል ።

በዚህም ምክንያት በ1957 ጆን ቻርልስ የተባለ የጁቬንትስ ሌጀንድ በ14 የመጀመሪያ የሴሪያ ጨዋታዎች 10 ግብ በማስቆጠር ይዞት የነበረውን ሪከርድ ተጋርቷል ።ከስድስት አስርት አመታት በኃላ መሆኑ ነው

ሴሪያውን ከተቆጣጠረች የሰነባበተችው አሮጊቷ ዘንድሮም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ካለው ናፖሊ 11 ነጥብ በመብለጥ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጣለች ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...