☀ማውሮ ኢካርዲ በዚህ ሰዓት ወደ ሪያል ማድሪድ መጓዝ እንደማይፈልግ ተናገረ።አርጀንቲናዊው አጥቂ በስፔኑ ክለብ በጥብቅ የሚፈለግ ሲሆን ሎስብላንኮዎቹ ከፍተኛ የሆነ የግብ አስቆጣሪ ችግር ስላለባቸው በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር እንደሚሞክሩ እየተዘገበ ይሆናል።ሆኖም ኢካርዲ ከኢንተር ጋር ዋንጫ ማሳካትን በቅድሚያ እንደሚፈልግ እና አላማው መሆኑን ተናግሯል ።
☀ፔፕ ጋርዲዮላ ፊፋ በተጨዋች ውሰት ጉዳይ ሊያወጣው ያሰበው ህግ ክለቡ ማንቸስተር ሲቲን እንደማያሳስበው ተናገረ።የአለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አለቃ (FIFA) አንድ ክለብ በውሰት ሊሰጣቸው የሚችለውን የተጨዋቾች ቁጥር ሊወስን ነው።ሆኖም ፔፕ ይህ ህግ እንደማያሰጋው ተናግሯል ።
☀ጁቬንትስ የፊዮሬንቲናውን የክንፍ አጥቂ ፌድሪኮ ቼሳ ለማዘዋወር በጥር ወር የዝውውር መስኮት ጥረት እንደሚያደርግ በርካታ የጣሊያን ጋዜጠኛ እያተቱ ነው።የ21 አመቱ ተጨዋች በግራም በቀኝም ክንፍ የመጫወት አቅም ያለው ሲሆን በበርካታ ጉምቱ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ከገባም ሰነባብቷል ።
በዋናነት ከጁቬንትስ በተጨማሪ የእንግሊዞቹ ሊቨርፑል እና ቼልሲ እንዲሁም የጣሊያኑ ናፖሊ ይፈልጉታል ።
☀ስሙ ከበርካታ ተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ጋር በመያያዝ ላይ የሚገኘው ባርሴሎና ዛሬ ደግሞ ስሙ በስፋት ከቶጎዋዊው የሄታፌ ተከላካይ ዲያን ያኮናም ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል ።
☀ቶተንሀም እና ማንቸስተር ሲቲ በቱሉዙ ታዳጊ አዲል ታዉዪ ጉዳይ ላይ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።የ17 አመቱ ተጨዋች ለፈረንሳዩ ክለብ U19 እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን በዚህ አመትም አምስት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል ።ቱሉዝ ለተጨዋቹ £4.5M ይፈልጋል ።
☀ቶተንሀም ከሁለት አመት በፊት ኢስኮን ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሶ እንደነበር ዴይሊ ሚረር አስነብቧል ።ስፔናዊው ኢንተርናሽናል የማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን ስብስብ ለመቀላቀል ሂደት ላይ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ የነበረው ዚነዲን ዚዳን በሳንቲያጎ በርናቢዮ እንዲቆይ አድርጎታል ።
☀ናፖሊ ማንቸስተር ዩናይትድ ለኩሊባሊ ያቀረበለትን €103M ውድቅ ማድረጉን Corriere dello sport አስነበበ።ቀውስ ላይ የሚገኙት ቀያይ ሰይጣኖቹ ለ27 አመቱ ተከላካይ ያቀረቡትን ሂሳብ የጣሊያኑ ክለብ ፕሬዚዳንት ኤላውሮ ደ ላውረንቲስ ወዲያውኑ ውድቅ አድርገውታል ተብሏል ።ካሊዱ ኩሊባሊ የክለቡ ቁልፍ ተጨዋች እንደሆነ ይታወቃል ።
☀ቼልሲ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን ተከላካይ ክርስቲያን ፑሉሲች እንደሚፈልገው Goal አስነብቧል ።ሰማያዊዎቹ ዶርትሙንድ የሚጠይቀውን £70M ለመክፈል ፈቃደኛ ባይሆኑም ከዛ በወረደ ዋጋ ገዝቶ በቼልሲ መቆየቱ ጥያቄ ውስጥ የገባውን የሀዛርድን ቦታ መተካት ይፈልጋሉ ።
☀ ዴቪድ ቪያ የቀድሞው የክለብ አጋሩ ኢኒየስታ ወዳለበት የጃፓኑ ክለብ ቪሰል ኮቤ ተዘዋውሯል ።ሁለቱ የቀድሞው የባርሴሎና ተጨዋቾች በካታላኑ ክለብ አይረሴ ጊዜን ማሳለፋቸው ይታወቃል ።
No comments:
Post a Comment