°ስሙ በስፋት ከዝውውር ጋር በመያያዝ ላይ የሚገኘው ኢስኮ ሪያል ማድሪድን በጥር ወር የዝውውር መስኮት እንደማይለቅ ተናገረ።ስፔናዊው የ26 አመት አማካይ ስሙ በስፋት ከእንግሊዙ
ክለብ ቼልሲ ጋር ሲያያዝ ነበር።
(Deportes Cuatro, via Metro)
°ማንችስተር ሲቲ የሪያል ቤቲሱን የግራ መስመር ተከላካይ ጁኒየር ፊርፖ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ከሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ፈተና ገጥሞታል።
(Mirror)
°የሊቨርፑሉ አጥቂ ዶሚኒክ ሶላንኬ የህክምና ምርመራውን በክሪስታል ፓላስ በማድረግ ላይ ይገኛል።የ21 አመቱ አጥቂ ወደ ሴል ሀረስት ፓርክ በውሰት ነው የሚዘዋወረው ።
(Mail)
°የ23 አመቱን የሊል ዊንገር ኒኮላስ ፔፔ ለማዘዋወር አርሰናል ፣ባርሴሎና እና ማንችስተር ሲቲ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።
(Le Voix du Nord, via Star)
°ራፋዔል ቫራን የእግር ኳስ ህይወቱን በሪያል ማድሪድ ለመጨረስ እንደሚያስብ Don Balon አስነብቧል ።ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ለቡድን አጋሩ ሰርጂዮ ራሞስ ጉዳዩን ነግሮታልም ተብሏል ።
°ቼልሲ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን የአጥቂ አማካይ ክርስቲያን ፑሉሲች በቀጣዩ
የዝውውር መስኮት ለማዛዋወር £45M አሰናድቷል።የጀርመኑ ክለብ ግን
የሌሎችን ክለቦች ፍላጎት በመመልከት አሜሪካዊውን ተጨዋች በተሻለ ገንዘብ
መሸጥ ይፈልጋል።
(ESPN)
°የኒውካስትሉ አሰልጣኝ ራፋ ቤኒቴዝ የሊድስ ዩናይትዱን አጥቂ ኬማር
ለማዛወር አቅደዋል።ቤኒቴዝ ተጨዋቹን ማዘዋወር የሚፋልጉት በጥር ወር
የዝውውር መስኮት ነው።
(Sunday Mirror)
°አዲሱ የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶልሻየር ስፔናዊው ግብ
ጠባቂ ዴቪድ ዴሄያ እና ፈረንሳዊውን አንቶኒዮ ማርሻል አዲስ ኮንትራት
እንዲፈርሙለት ይፈልጋል።ለማንችስተር ዩናይትድ የበላይ አመራሮችም
አሳውቋቸዋል።
(Mail on Sunday)
°ጣሊያናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ማቲዮ ዳርሚያን በሴሪያዎቹ
ክለቦች ኢንተር ሚላን እና ላዚዮ ይፋለጋል።
(Calciomercato)
°አርሰናል በቶተንሀም በጥብቅ የሚፈለገውን የኖርዊች ሲቲውን የ18 አመት
ታዳጊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።
(Sunday Mirror)
°ሊቨርፑል ቱርካዊውን የ19 አመት የአጥቂ አማካይ አብዱልቃድር ኡመር
የማስፈረም ፍላጎት አለው።ሮማ እና ማንችስተር ሲቲም የተጨዋቹ ፈላጊዎች
ናቸዉ ።
(Fotomac, via Star on Sunday)
°የ33 አመቱ የቶተንሀም አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ በጥር ወር የዝውውር
መስኮት ወደ ቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ለመዘዋወር በግሉ ከስምምነት ላይ
ደርሷል።
(Turkish outlet Star, via Sun on)
Good presentation.
ReplyDelete