"ትላልቅ ተጨዋቾችን መግዛት በተለይ ለማንቸስተር ዩናይትድ ከባድ ነው " ሞሪንሆ
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ፉክክሩ በማየሉ ምክንያት ትላልቅ ተጨዋቾችን ማዘዋወር አዳጋች እንደሆነ ተናገሩ።
የቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ከአመት አመት ትላልቅ ተጨዋቾችን የማስፈረም ጉዳይ በተፎካካሪዎች መጨምር ምክንያት ከባድ ነው ብለዋል ።
ማንቸስተር ዩናይትድ በዘንድሮው አመት ከ13 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ስድስቱን ብቻ ያሸነፈ ሲሆን ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ፤ ይህ ደግሞ አሰልጣኙ ላይ ጫናን አሳድሯል ።
አወዛጋቢው አሰልጣኝ ይህንን አስተያየት የሰጡት በክለባቸው ቀውስ ምክንያት ደጋፊዎች በጥር ወር የዝውውር መስኮት ተጨዋቾች እንዲመጡ ጫና እያሳደሩ መሆኑን ተከትሎ ነው።
ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ ሳውዝሀምተንን ይገጥማል ።
No comments:
Post a Comment