¤የቼልሲው አማካይ ሴስክ ፋብሪጋስ በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በቼልሲ እንደሚቆይ ተናገረ።ስፔናዊው የ31 አመት ስፓኒያርድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በርካታ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ያቀርቡልኛል ብሎ እንደሚያስብም ተናግሯል ።
(Talksport)
¤ባርሴሎና ያለበትን የተከላካይ መስመር ችግር ለመፍታት የ32 አመቱን ቤልጄሚያዊ የማንቸስተር ሲቲ ተከላካይ ቪንሰንት ኮምፓኒ እና ሰርቢያዊውን የዜንት ፒተርስበርክ የ34 አመት ተከላካይ ብራንስላቭ ኢቫኖቪች እቅዱ ውስጥ ከቷል ።የካታላኑ ክለቡ ከሁለቱ አንዱ ተጨዋች በጥር ወር የዝውውር መስኮት በማዘዋወር ለአጭር ጊዜ እስከ አመቱ መጨረሻ ለመጠቀም አቅዷል ።
(Mirror)
¤ሪያል ማድሪድ ስፔናዊውን የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ኢብራሂም ዲያዝ ለማዘዋወር ጠንክሮ እየሰራ ነው።የ19 አመቱ ተጨዋች በእንግሊዝ ህይወት አልጋ በአልጋ አልሆነለችለትም።
(AS - in Spanish)
¤ኢንተር ሚላን የ22 አመቱን ብራዚላዊ የክንፍ አጥቂ ጋብሬል ባርቦሳ ወደ ሳንቶስ በውሰት ለመሸኘት መዘጋቱ ተዘግቧል ።በ38 ጨዋታዎች 22 ግቦችን ያስቆጠረው ብራዚላዊ ኮከብ በእንግሊዞቹ ኤቨርተን ፣ዌስትሀም እና ክሪስታል ፓላስ በጥብቅ ይፈለጋል ።
(Mail)
¤ቼልሲ ባርሴሎና ዴንማርካዊውን ተከላካይ ክርስቲያንሰን ለማዘዋወር ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ።ባርሴሎና የ22 አመቱን ተከላካይ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማስፈረም ይፈልጋል ።
(Mirror)
¤የዴቪድ ዴሄያ ወኪል የሆነው ጆርጌ ሜንዴዝ ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ በኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት ቁልፉ ሰው መሆኑን ጆዜ ሞሪንሆ ተናግረዋል ።የ28 አመቱ ግብ ጠባቂ በማንቸስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ አመት እስከ 2020 የሚያቆየውን ኮንትራት በቅርቡ መፈረሙ ይታወሳል ።
ሆኖም ረዥም ኮንትራት ለመፈረም የጆዜ ሞሪንሆን ቆይታ ማወቅ ይፈልጋል ተብሏል ።
(Star)
¤የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ከስምንት አመታት በፊት ማንቸስተር ሲቲ ለማዘዋወር ጠይቆት እንደነበር ተናገረ።በአሁኑ ሰዓት በሜጀር ሊግ ሶከር የሚገኘው ኢብራ ካዳብራ በወቅቱ በባርሴሎና አሰልጣኝ የነበረው ፔፕ ጋርዲዮላ ፈልጎት አዘዋውሮትም ነበር ።
(Sun)
¤ክሮሺያዊው የ29 አመት ተጨዋች ኢቫን ፔሪሲች ባሳለፍነው አመት ከኢንተር ሚላን ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመዘዋወር ፈልጎ እንደነበር ተናግሯል ።ቀያይ ሰይጣኖቹ አሁንም ቢሆን ተጨዋቹ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የሚታወቅ ነው።
(FourFourTwo)
በዚህ ሳምንት በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚደረጉ
ጨዋታዎች መርሀግብር
የእንግሊዝ ፕርሜርሊግ
አርብ| ካርዲፍ ሲቲ 5:00 ወልቨርሃምፕተን
ቅዳሜ| ክሪስታል ፓላስ 12 : 00 በርንሌ
ቅዳሜ| ሀደልስፊልድ 00 : 00 ብራይተን & ሆቭ አልቢዮን
ቅዳሜ| ሌስተር ሲቲ 12 : 00 ዋትፎርድ
ቅዳሜ| ማንችስተር ሲቲ 12: 00 በርንስማውዝ
ቅዳሜ| ኒውካስል ዩናይትድ 00 : 00 ዌስትሀም ዩናይትድ
ቅዳሜ| ሳውዝሀምፕተን 02 : 30 ማንችስተር ዩናይትድ
እሁድ| ቸልሲ 9 : 00 ፉልሀም
እሁድ| አርሰናል 11 : 05 ቶተንሀም ሆስፐር
እሁድ| ሊቨርፑል 01 : 15 ኤቨርተን
የጀርመን ቡንደስሊጋ
አርብ| ፎርቱን ዶስልዶርፍ 4:30 ሜንዝ 05
ቅዳሜ| ቦርሲያ ዶርትመንድ 11 : 30 ፍራይቡርግ
ቅዳሜ| ስቱትጋርት 11: 30 ኦግስበርግ
ቅዳሜ| ወርደርብሬመን 11 : 30 ባየርሙኒክ
ቅዳሜ| ሀኖቨር 96 11: 30 ኸርታ በርሊን
ቅዳሜ| ሆፈኔም 02 : 30 ሻልካ 04
እሁድ| አርቢላይፕዚክ 23 : 30 ቦርሲያሞንቸግላድባክ
እሁድ| ኢንትራንክ ፍራንክፈርት 02 : 00 ወልፍስበርግ
ሰኞ| ኑረምበርግ 04 : 30 ባየርሊቨርኩሰን
ስፔን ላሊጋ
አርብ| ሪዮ ቫይካኖ5:00ኢባር
ቅዳሜ| ሴልታቪጎ 9 : 00 ሁሴክ
ቅዳሜ| ሬያል ቫላዶሊድ 12 : 15 ሌጋነስ
ቅዳሜ| ጌታፌ 02 : 30 ኢስፓኞል
ቅዳሜ| ሬያል ማድሪድ 04 : 45 ቫሌንሺያ
እሁድ| ሬያልቤቲስ 8 : 00 ሬያል ሶሲዳድ
እሁድ| ጄሮና 00 : 15 አትሌቲኮ ማድሪድ
እሁድ| ባርሴሎና 02 : 30 ቪያርያል
እሁድ| ዲፖርቲቮ አላቬስ 04 : 45 ሲቪያ
ሰኞ| ሌቫንቴ 05 : 00 አትሌቲኮ ቢልባኦ
ፈረንሳይ ሊግ -1
አርብ| ሴንቲቴን 04 : 45 ናንትስ
ቅዳሜ| ሊል 01 : 00 ኦሎምፒክ ሊዮን
ቅዳሜ| አንገር 04 : 00 ኬን
ቅዳሜ| ገንገው 04 : 00 ኒስ
ቅዳሜ| ሞናኮ 04 : 00 ሞንፔሌ
ቅዳሜ| ኒምስ 04 : 00 አሜንስ
እሁድ| ቱሉስ 23 : 00 ዲጆን
እሁድ| ኦሎምፒክ ደማርሴ 01 : 00 ሬምስ
እሁድ| ሬንስ 01 : 00 ስትራስቡርግ
እሁድ| ቦርዶ 05 : 00 ፓሪሴን ጀርመን
የጣልያን ሴሪያ
ቅዳሜ| ስፓል 11 : 00 ኢምፖሊ
ቅዳሜ| ፊዮረንቲና 02 : 00 ጁቬንቱስ
ቅዳሜ| ሳምፒዶሪያ 04 : 30 ቦሎኛ
እሁድ| ኤስሚላን 8 : 30 ፓርማ
እሁድ| ፍሮሶኔ 11 : 00 ካግላሪ
እሁድ| ሳሱሎ 11 : 00 ኡዲኒዜ
እሁድ| ቶሪኖ 11: 00 ጄኖዋ
እሁድ| ቼቮ 02 : 00 ላዚዮ
እሁድ| ሮማ 04 : 30 ኢንተርሚላን
ሰኞ| አትላንታ 04 : 30 ናፖሊ
No comments:
Post a Comment