ማንቸስተር ዩናይትድ የዴቪድ ዴሄያን ውል እስከ 2020 አራዘመ
ከሰዓታት በፊት በወጣ መረጃ ዴቪድ ዴሄያ እስከ 2020 በማንቸስተር ዩናይትድ የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።
ስፔናዊው ኢንተርናሽናል 2015 ላይ የአራት አመት ኮንትራት የፈረመ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ የፈረንጆቹ አዲስ አመቱ ውሉ ያልቅ ነበር ።በተለይ የዝውውር መስኮቶች በተከፈቱ ቁጥር ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር በተደጋጋሚ ይያያዝ ነበር።
ሆኖም ዛሬ ከሰዓት የተሰማው መረጃ የቀያይ ሰይጣኖቹን ደጋፊዎች በመጠኑም ቢሆን አስደስቷል ።
No comments:
Post a Comment