ቺሊያዊው ኢንተርናሽናል አሌክሲስ ሳንቼዝ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከማንቸስተር ዩናይትድ ሊሰናበት እንደሚችል እየተዘገበ ነው።የ29 አመቱ አጥቂ ከአርሰናል ከተዘዋወረ አንስቶ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ስኬት ርቆታል። በዚህም ምክንያት ከክለቡ የመልቀቅ ፍላጎት ያለው ሲሆን ሞሪንሆም ቢለቅ አይሰፉም።
(ሚረር)
በውድድሩ አመት መጨረሻ ውሉ የሚያልቀው የቶተንሀሙ አማካይ ሙሳ ዴምቤሌ በበርካታ ክለቦች ይፈለጋል ።በዋናነት የጣሊያኖቹ ጁቬንትስ እና ኢንተርሚላን የ31 አመቱ ቤልጄሚያዊ ፈላጊዎች ናቸው።
(ካልሺዮ መርካቶ)
ባየርን ሙኒክ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የቼልሲውን ከ17 አመት በታች የአለም ዋንጫ አሸናፊ ካለም ሁድሰን ኦዶው ለማዘዋወር ከአሁኑ እየሰራ ነው
(ሜል)
ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ዠርደን ሻኪሪ በሊቨርፑል ደስተኛ እንደሆነ ተናገረ።የ27 አመቱ ተጨዋች በዠርደን ክሎፑ ቡድን ውስጥ በቋሚነት የመሰለፍ ዕድል ማግኘትን ባይችልም መቆየት እንደሚሻ ነው የተናገረው ።የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን የተጨዋቹ ቀንደኛ ፈላጊ ነው።
(ላጋዜታ ዴሎ ስፖርት)
ኒውካስትል ዩናይትድ የ24 አመቱ የአታላንታ ተጨዋች ሚጉዌል አልሚሮን ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ።ፓራጓዊው አማካይ በጣሊያን አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ላይ ይገኛል ።
(ሜል)
(ሚረር)
ከዝውውር ውጪ ያሉ መረጃዎች
- ትናንት በሻምፒዮንስ ሊግ ግብ ማስቆጠር የቻለው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ በአንድ ክለብ በርካታ ግብ ያስቆጠረ ተጨዋች ሆኗል
No comments:
Post a Comment