Thursday, November 29, 2018

አይረሴው የጆን ቴሪ ምሽት ሞስኮ 2008






በሮማን አብረሀሞቪች ዘመን የቼልሲ ወደ አለማችን ሃያልነት ሲቀየር ከመጡ አይረሴ ድሎች ከማይዘነጉ አሳዛኝ ሽንፈቶች በስተጀርባም ሚስተር ቼልሲ ዋናው ምልክት ነው።

ማን ያንን የተረገመ ምሽት ይረሳል?
2008 ሞስኮ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ በዝናባማው ምሽት ቴሪ ያጋጠመውን እድሜ ዘመኑን እንደማይረሳው ይናገራል ።ሚስተር ቼልሲ የሚወደውን ክለብ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድል ሊያበቃ ለመለያ ምት ወደ ቫንደርሰን መረብ እየተንደረደረ ነው

 ካስቆጠረው ሁሉም ነገር ያበቃል ቼልሲም ለመጀመሪያ ጊዜ በአብረሀሞቪች አቢዮት ሻምፒዮን ይሆናል

ሰውየው እግርኳስን እንዲወዱ ምክንያት የሆናቸውን ያ የማንቸስተር እና ማድሪድ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እያሰቡ በቪ አይ ፒ ቦታቸው በስሜት ተውጠው ተቀምጠዋል 

አላውቅም ተንሸራተትኩ ኳሷን በጨረፍታ አገኘኋት የቼልሲ ደጋፊዎችን ህልም ገደል ከተትኩ የጓደኞቼን አይን ማየት አፈርኩ ቼልሲን እንደከዳሁት ተሰማኝ በዛ ምሽት ሳለቅስ አደርኩ ያንን ምሽት ማስታወስ አልፈልግም የሞስኮ ፍፃሜ 2005 በግማሽ ፍፄሜ የተሸነፍንበት እንዲሁም የካምፕ ኑ ቀይ ካርድ ታላቁን የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ሳስብ በህሊናዬ ላይ ይደቀናሉ

በፍፃሜው በቅጣት ባልጫወትም የ2011 ድላችን ግን እነዛን አስከፊ ምሽቶች ያስረሳኛል።
ድሮግባ ፔናሊቲውን ሊመታ ሲንደረደር የሞስኮው ክስተት ትዝ አለኝ አይኔን ጨፈንኩ ነገር ግን ሁሉም ነገር በድል ተቀየረ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...