የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ ሊ ሻርፕ በኦሌ ጉናር ሶልሻየር ቡድን ደስተኛ መሆኑን ተናግሮ ፤ ሆኖም ሁነኛ አጥቂ ግን እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።
ከቀናት በኋላ በሚከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮትም ሊ ሻርፕ ኤሪሊንግ ሀላንድ ወይም ሀሪ ኬን ኦልድ ትራፎርድ መክተም አለባቸው ብሏል።
ሻርፕ ከላይ ከተጠቀሱት አጥቂዎች አንዱን ቀያይ ሰይጣኖቹ ካስፈረሙ እነ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ማርሻል በተሻለ ተነሳሽነት ለመሰለፍ ስለሚጫወቱ ቡድኑ የተሻለ ይጠቀማልም ብሏል።
አስደናቂ አቋም ላይ የሚገኘው ዩናይትድ ከመሪው ሊቨርፑል እኩል 33 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
No comments:
Post a Comment