Saturday, January 2, 2021

የዕለተ ቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች


አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ 



 ማርሴዎች በዚህ አመት ከናፖሊ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን አጥቂውን አርካዜክ ሚሊክን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው reports Gazzetta dello Sport አስነብቧል።ሚሊክን ከማርሴይ በተጨማሪ አትሌቲኮ ማድሪዶችም የኮስታ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋሉ። 






ፒኤስጂዎች ማውሪዚዮ ፖቸቲንሆን ዛሬ ማምሻውን በይፋ አሰልጣኝ እንደሚያደርጉት የፈረንሳዩ L'Equipe አስነብቧል። እንደ ምክንያት የቀረበውም ፒኤስጂዎች ከእረፍት መልስ እሁድ ወደ ልምምድ ይመለሳሉ።ስለሆነም ፖቸቲንሆን ዛሬ በይፋ አሰልጣኝ እንደሚያረጉት ይጠበቃል። 





አርሰናሎች በጥር የዝውውር መስኮት የሜሱት ኦዚል ተተኪ ለማግኘት ወደ ገበያ እንደሚወጡ ተሰምቷል። የረጅም ጊዜ ኢላማቸው የነበረው የአዋር ዝውውር እንደማይሳካ ስላወቁ አሁን ላይ ፊታቸውን ወደ ቦሩሲያ ዶርትመንዱ ጁሊያን ብራንት ማዞራቸውን Sport Witness አስነብቧል። 





ሪያል ማድሪዶች የሶስት ተጨዋቾቻውን ኮንትራት ለማደስ ድርድር ላይ መሆናቸውን ዚዳን ይፋ አድርጓል። ማድሪዶች በዚህ አመት ኮንትራታቸው የሚጠናቀቀውን የራሞስ ሞድሪች ቫዝኬስ ኮንትራት ለማደስ ንግግር ላይ ሲሆኑ አላባንም በነፃ ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸው ታውቋል። 






የወልቭሱ አሰልጣኝ እስፕሪንቶ የአትሌቲኮውን ዲያጎ ኮስታ እና የሊቨርፑሉን ዋይናልደምን በጥር እና በክረምት ዝውውር መስኮቶች በነፃ ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ዘሰን አስነብቧል። 






ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና በቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ዝውውር ላይ መፋጠጣቸውን AS አስነብቧል። ማድሪዶች በክረምት ዋነኛ የዝውውር ኢላማቸው ሀላንድ እንደሆነ ታውቋል።በተጨማሪም ባርሴሎናዎች ያለባቸውን የፊት መስመር ተጨዋች በሀላንድ ለመሙላት ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል። 






ማንችስተር ዩናይትዶች በጥር የዝውውር መስኮት ሁለት ትላልቅ ዝውውሮችን ለመፈፀም መዘጋጀታቸውን M.E.N አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ዩናይትዶች ዋነኛ ኢላማቸው የዶርትመንዱ የመስመር አጥቂ ጃደን ሳንቾ እና የሌብዢኩ ኡፓምካኖ መሆናቸው ተነግሯል። 






ቸልሲዎች ሁለት ተጨዋቾችን ወደ ብሪጅ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው London Standard አስነብቧል። ቸልሲዎች በመጀመሪያ የተከላካይ ስፍራቸውን ለማጠናከር የስትራስቡርጉን ተከላካይ ሞሀመድ ሲማካን ሲፈልጉ ተጨዋቹ በኤሲሚላን እና ኒስም ይፈለጋል። በተጨማሪም የዌስትሀም ዩናይትዱን አማካይ ዴክላን ራይስንም ማስፈረም ይፈልጋሉ። 






ኤቨርተኖች ውሉ በ2022 ለሚጠናቀቀው አይስላንዳዊ አማካይ ገልፊ ሲጉድሰን አዲስ ኮንትራት ውል እንዳቀረቡለት ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። በ2017 በ£45m ከስዋንሲ ሲቲ ያስፈረሙት ሲጉድሰን በኤቨርተን ቤት ጥሩ ሚባል ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን አዲሱን ኮንትራት እንደሚፈርምም ይጠበቃል። 





ማንችስተር ዩናይትድ እና ዳኒኤል ጀምስ ለመለያየት መቃረባቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። ጄምስ ዩናይትድን በውሰት ይሁን በቋሚ በምን እንደሚለቅ ይፋ ባይሆንም በጥር ግን ዩናይትድን መልቀቁ እርግጥ ሆኗል። ሊድስ እና ዌስትብሮም ልጁን በጥብቅ ይፈልጉታል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...