Wednesday, January 6, 2021

ማርዮ ባሎቴሊ እና ዘረኝነት





 ✅ማርዮ ባሎቴሊ በአንድ ወቅት አውሮፓ ለተወለዱ ግን አፍሪካዊ የዘር ሀረግ ላላቸው ሰዎች የመከረው


"ለነሱ ፤ ጨዋታ ስታሸንፍ አውሮፓዊ ነህ።ስትሸነፍ ግን አፍሪካዊ ነው።አዎ ብዙዎች ይሄ አጋጥሞናል።የሚገርመው ከአሰልጣኞች ፣ ከደጋፊዎች ፣ ከቡድን አጋሮችህም ጭምር ይህ ይደርስብሃል።

ወጣት ሆነው ለአፍሪካዊ እና አውሮፓዊ ሀገር የመጫወት ዕድል ላላቸው ሰዎች የምመክረው ፤ መገለልን ፣ መገፋትን ፣ ዘረኝነትን መቋቋም ከቻላችሁ ለአውሮፓ ተጫወቱ።ነገር ግን ለሰራችሁት ምስጋና እና እውቅና ማግኘትን ከፈለጋችሁ ለአፍሪካ ተጫወቱ።


ለአውሮፓ ስለተጫወትክ ታላቅ ተጨዋች ትሆናለህ የሚለው ውሸት ነው።ድሮግባን ፣ ኤቶን ፣ ቱሬን ፣ ጆርጅን እንደ ምሳሌ ማየት ይቻላል ።እነዚህ ለሀገራቸውም ለክለብም ስኬታማ ነበሩ።የዓለም ዋንጫን በአውሮፓም ሻምፒዮንስ ሊግን መጫወት ችለዋል።


ጣሊያን ለኔ ላደረገችልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ።ሆኖም ድጋሚ የመጫወት ዕድሉ ቢሰጠኝ ለጋና ነው የምጫወተው።"

ማርዮ ባሎቶሊ


 

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...