ሪያል ማድሪዶች የመሀል ክፍላቸውን ለማጠናከር የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ የሬንሱን ፈረንሳዊ አማካይ ኤዱአርዶ ካማቪጋን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት ማሳየታቸውን AS አስነብቧል።
የዴቪድ ቤካም ንብረት የሆነው የMLS ክለብ የሆነው ኢንተር ሚያሚ የኤቨርተን ተጠባባቂ በረኛ የሆነውን ዴንማርካዊውን ጆናስ ሎስልን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው Miami Herald አስነብቧል። በተጨማሪም የዩናይትዱን ሮሜሮንም ይፈልጉታል።
ጣሊያናዊው የቸልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ክለቡን በጥር የዝውውር መስኮት ለመልቀቅ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡን LONDON EVENING አስነብቧል።ተጨዋቹም ወደ ሀገሩ ክለቦች ተመልሶ የመጫወት ትልቅ ፍላጎት እንዳለው እና ወደ ሴሪያው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑ ታውቋል።
አርሰናሎች የበርናንድ ሌኖ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ገበያው እንደወጡ ዴቪድ ኦርነስቲን ይፋ አድርጓል። እስካሁን በይፋ የተደረገ ንግግር ባይኖርም አርሰናሎች በቀጣይ ቀናት አንድ ግብ ጠባቂ እንደሚያስፈርሙ እርግጥ ሆኗል።
ማንችስተር ዩናይትዶች የፈረንሳዊውን ኮከብ የፖል ፖግባን መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።ዩናይትዶች ፖግባን ፈልጎ ለሚመጣ ክለብ እስከ £75m መክፈል እንዳለባቸው ሲናገሩ ከሰሞኑ የልጁ ፈላጊ ሆነው ለመጡት ፒኤስጂዎች ዋጋው እንዳልተወደደባቸው እና ልጁን £75m ከፍለው እንደሚወስዱት ተማምነዋል።
ጄኑዋዎች በቀጣይ ቀናት ውስጥ የአርሰናሉን ተከላካይ ግሪካዊውን ሶቅራጠስ ፓፓስቶፖሎስን እንደሚያስፈርሙት የክለቡ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ አሌሳንድሮ ዛርባኖ ትናንት ተናግረዋል። ተጨዋቹ ከአርሰናል እንደሚለቅ የታወቀ ሲሆን በመጨረሻም መዳረሻው የጣሊያኑ ጄኑዋ ለመሆን ተቃርቡዋል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በጥር የዝውውር መስኮት ሁለቱን ወጣት የመሀል ተከላካይ እና የቀኝ መስመር ተከላካይ የሆኑትን የሊሉን ቦባክሪ ሶማሬ እና የኖርዊቹን ማክስ አሮንስን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።ሊሎች ሱማሬ ላይ £35m ለጥፈውበታል።
አርሰናሎች የመሀል ክፍል ፈጠራ ችግራቸውን ለመቅረፍ ወደ ገበያ ወተዋል። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረታቸው የሆነውን የኖርዊቹን አማካይ ኤሚ ቡኤንዲያን ለማስፈረም ከኖርዊች ጋር ግንኙነት መጀመራቸውን Fabizio Romano አረጋግጧል። ኖርዊቾች ከተጨዋቹ ዝውውር £40m ይፈልጋሉ።
ኢኳዶሪያዊው አማካይ ሞሰስ ካሲዶ በዚህ ሳምንት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ እንደሚዘዋወር የክለቡ ዳይሬክተር ይፋ አድርገዋል። ወዴት እንደሚያመራ ይፋ ባያረጉም ግን ተጨዋቹ ብቸኛ ፈላጊው ወደ ሆነው ብራይተን እንደሚያመራ እርግጥ ሆኗል።
በናፖሊ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘው እና የቸልሲ ንብረት የሆነው ፈረንሳዊው አማካይ ቲሞ ባካዮኮ በኔፕልሱ ክለብ ደስተኛ እንደሆነ እና ቋሚ ውልም መፈረም እንደሚፈልግ ወኪሉ ተናግሯል።
Betam arif nw ketlbet
ReplyDelete