Monday, January 11, 2021

የዕለተ ሰኞ ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ 




 ኒውካስትል ዩናይትድ እና ዌስትሀም ዩናይትድ በስፔዚያው የ24 አመት አጥቂ ባላ ዞላ ላይ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው Calcio Mercato አስነብቧል።ተጨዋቹ በናፖሊም ይፈለጋል። ሁለቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ግን ተጨዋቹን በጥር ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። 






ለቶተንሀሙ አማካይ ሀሪ ዊንክስ የውሰት ጥያቄ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ቫሌንሲያዎች የኖርዊቹ አማካይ ኤሚ ቡኤንዲያ ዝውውር ላይ መግባታቸውን La Razon አስነብቧል።አርሰናሎች ተጨዋቹን ለማስፈረም ንግግር የጀመሩ ቢሆንም አሁን ላይ ቫሌንሲያዎች ዝውውሩ ላይ በይፋ ገብተዋል።ኖርዊቾች ከተጨዋቹ ዝውውር እስከ £40m ይፈልጋሉ። 






አትሌቲኮ ማድሪዶች የፈረንሳዊውን የሊዮን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌን ዝውውር መጨረሳቸው ታውቋል።እንደ ፈረንሳዩ ሌኪፕ ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ  ዛሬ ወደ ስፔን በመጓዝ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ እና በይፋ አትሌኮን እንደሚቀላቀል ታውቋል።ዴምቤሌ አትሌቲን ሚቀላቀለው በውሰት ነው። 





ኤሲ ሚላኖች የሁለቱን ኮኮቦቻቸው ኮንትራት ለማራዘም ንግግር ላይ መሆናቸውን ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል። ሁለቱ ኮከቦች ግብ ጠባቂው ዶናሩማ እና አማካዩ ቻኑጉሎ ሲሆኑ የሁለቱም ኮንትራት በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራታቸው ይጠናቀቃል። 





ቤኔፊካዎች ፖርቱጋላዊውን አማካይ ዊሊያም ካርቫልሆን ከሪያል ቤትስ ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸውን የፖርቱጋሉ O Jogo አስነብቧል።ከ2018 ከስፖርቲንግ ሊዝበን አስፈርመውት ጉዳት እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ሪያል ቤትሶች ለተጨዋቹ እስከ £16m ከቀረበላቸው ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው። 






ማንችስተር ዩናይትዶች ሙሉ በሙሉ ከኢኳዶሪያዊው የ19 አመት አማካይ ሞሲስ ካሲዶ ዝውውር መውጣታቸውን ስካይ ስፖርት አረጋግጧል። ተጨዋቹ ባሳለፍነው ሳምንት ዩናይትድን ሊቀላቀል ይችላል ቢባልም አሁን ላይ ግን እራሳቸውን ከዝውውሩ አውጥተዋል። አሁን ላይ ብራይተኖች አዲሱ የካሲዶ ፈላጊ ሆነው መተዋል። 






ዌስትሀም ዩናይትዶች ብራዚላዊውን የሪያል ማድሪድ የ27 አመት የመስመር አጥቂ ማርያኖ ዲያዝን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። ዌስትሀሞች ሀለርን ለመተካት ከበርካታ ተጨዋቾች ጋር ስማቸው እየተነሳ ነው። 






ሪያል ቤትሶች የሳውዝሀምተኑን የ21 አመቱን የመስመር ተጨዋች ዳን ሉንዱሉን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት ማሳየታቸውን Todofichajes አስነብቧል።ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን ለሳውዝሀምተን ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን አድርጓል። 






ኤቨርተኖች በፖርቶ በውሰት እያሳለፈ የሚገኘውን የዌስትሀም ዩናይትድ ንብረት ፊሊፔ አንደርሰንን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው TeamTalk አስነብቧል። በፖርቶ ደስተኛ ያልሆነው አንደርሰን ወደ እንግሊዝ መመለስ ይፈልጋል።ይህንንም ተከትሎ ኤቨርተኖች ልጁን ለመውሰድ ዝግጁ ሆነዋል። 





አርሰናሎች ለእንግሊዛዊው የ25 አመት የመሀል ተከላካይ ሮብ ሆልዲንግ የተሻሻለ አዲስ ኮንትራት ማቅረባቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ተጨዋቹ በአርቴታ የረጅም አመት እቅድ ውስጥ ስለሚገኝ በቀጣይ ሳምንታት ኮንትራቱን ያራዝማል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...