ዌስትሀም ዩናይትዶች ከቀናት በፊት ወደ አያክስ የሸኙትን ሴባስቲያን ሀለርን እንደሚተኩ አሰልጣኙ ሞይስ አረጋግጠዋል።እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ ደሞ ዌስትሀሞች አሁን ላይ ዋነኛ ኢላማቸው ያረጉት ወጣቱን የአርሰናል አጥቂ ኤዲ ኒኪታህ መሆኑ ታውቋል።
ቶተንሀሞች የተከላካይ መስመራቸውን ለማጠናከር ፊታቸውን ወደ ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ኤደር ሚሊታዎ ማዞራቸውን AS አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ሚሊታኦም በቤርናባው ደስተኛ አይደለም። ይህንን ተከትሎ የጆዜው ቶተንሀም ልጁን የማግኘት እድል አለው።
ቸልሲዎች ፍራንክ ላምፓርድን በቀጣይ የሊግ ጨዋታ ውጤቱን በማየት የተሻለ ነገር ካላሳየ በማሰናበት ተተኪ ሌላ አሰልጣኝ ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው London Evening አስነብቧል።ቸልሲዎች የቀድሞውን የጁቬንቱስ አሰልጣኝ አሌግሪ በቅርቡ ከፒኤስጂ የተሰናበተውን ቱሄልን የሌብዢኩን ኔግልስማን የሳውዛንብተኑን ሀሰንሁተልን ላምፓርድን ለመተካት ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋል።
በዚህ አመት በይፋ ከማንችስተር ሲቲ ሚለቀው ብራዚላዊው የ33 አመቱ ፈርናንዲንሆ ከተለያዩ የአውሮፓ እና የብራዚል ክለቦች በርካታ የእናስፈርምህ ጥያቄ እየቀረበለት እንደሆነ ወኪሉ ይፋ አድርጓል።ፈርናንዲንሆ በ2013 ከሻካታር ነበር ሲቲን የተቀላቀለው።
ፊዮሬንቲናዎች በአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን የአርሰናሉን ኡራጋዊ አማካይ ሉካስ ቶሬራን በአመቱ መጨረሻ ማስፈረም እንደሚፈልጉ Mundo Deportivo አስነብቧል። ፊዮሬንቲናዎች ተጨዋቹን ማስፈረም የሚፈልጉት በቋሚ ዝውውር ነው።
አትሌቲኮ ማድሪዶች የሊዮኑን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።በተጨማሪም እንደ Football Insider ዘገባ ከሆነ ደግሞ ዴምቤሌን ለማስፈረም ከወኪሉ ጋር ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል።
ቸልሲዎች በፈረንሳንሳዊው የአርቢ ሌብዢክ ተከላካይ ዳዮት ኡፓምካኖ ዝውውር ላይ እንደገቡበት ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።ቸልሲዎች ልጁን በክረምት የዝውውር መስኮት ዋነኛ ኢላማቸው አድርገውታል።ኡፓምካኖ ከቸልሲ በተጨማሪ በሊቨርፑል እና በማንችስተር ዩናይትድ ይፈለጋል።
ኢንተር ሚላኖች በጥር ዝውውር መስኮት አማካያቸውን ክርስቲያን ኤሪክሰንን ሚሸጡት ከሆነ የማንችስተር ዩናይትዱን አማካይ ጄሲ ሊንጋርድን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ኢንተሮች ከሊንጋርድ በተጨማሪ የፒኤስጂውንም ፓራዴዝ ማስፈረም ይፈልጋሉ።
አዲሱ የፒኤስጂ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ፖቸቲንሆ ከኤሪክሰን ይልቅ ዋነኛ ምርጫቸው የማንችስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ እንደሆነ ሌኪፕ አስነብቧል። ተጨዋቹ ኮንትራቱ በ2022 ሚጠናቀቅ ሲሆን በክረምቱ ፖቸቲንሆ እንዲመጣለት ጥያቄ አቅርቧል።
እንግሊዛዊው አማካይ ዴክላን ራይስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ከመዘዋወር ይልቅ እዛው በለንደን መቆየትን መምረጡን London Evening አስነብቧል።ይህንን ተከትሎ የልጁ ሌላኛ ፈላጊ የሆኑት ቸልሲዎች ልጁን በቀላሉ እንደሚያገኙት ተማምነዋል።
No comments:
Post a Comment