Monday, December 28, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

 ራዎል ሂሚኔዝን በጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ እንደሚያጡት ያረጋገጡት ወልቭሶች በጥር የዝውውር መስኮት የተለያዩ ተጨዋቾችን መመልከት ጀምረዋል። እንደ The Athletic ዘገባ ከሆነ ኑኖ እስፕሪንቶ የመጀመሪያ ምርጫቸው ክሮሺያዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ሉካ ዮቪች ሆኗል። 





ማውሪሲዮ ፖቸቲኖን ለመቅጠር ከጫፍ የደረሱት ፒኤስጂዎች በጆዜ ስር የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘውን እንግሊዛዊውን ዴሊ አሊን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Foot Mercato አስነብቧል። በተጨማሪም ኤሪክሰንንም ለማምጣት ይፈልጋሉ። 






የኦዚል ወኪል እና ጁቬንቱስ ግንኙነት መጀመራቸውን Tuttosport አረጋግጫለው ብሏል። ጁቬዎች ተጨዋቹን በአመቱ መጨረሻ በነፃ ከማስፈረም ይልቅ በጥር ዝውውር መስኮት እስከ £10m በማውጣት ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል። 





አራቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዌስትብሮሚች፣ ሊድስ ብራይተን፣ በርንሌይ ዌልሳዊውን የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ዳንኤል ጀምስን ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው The Daily Star አስነብቧል። ተጨዋቹ በጥር ዩናይትድን ለመልቀቅ እንደሚገደድ ታውቋል። ምክንያቱም በቦታው ተጨማሪ ተጨዋች ዩናይትድ እንደሚያስፈርም እርግጥ ስለሆነ። 




አርሰናሎች የረጅም ጊዜ የሄክተር ቤለሪን ተተኪ እንዲሆንላቸው የብራይተኑን የመስመር ተከላካይ ታሪቅ ላምፕቴን ለማስፈረም ከብራይተን ሰዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን Mirror አስነብቧል። ተጨዋቹ በማንችስተር ሲቲ እና ባየርን ሙኒክም ይፈለጋል። 





ቶተንሀሞች በድጋሚ የቀድሞ ኮከባቸውን ክርስቲያን ኤሪክሰንን ወደ ለንደን ለመመለስ ጥረት መጀመራቸውን Calciomercato አስነብቧል። በጥር ኢንተርን እንደሚለቅ ሚጠበቀው ኤሪክሰን በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ይመለሳል ተብሎ ባይጠበቅም ቶተንሀሞች ግን ልጁን ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው። 





ሪያልማድሪዶች ከሁለቱ የማንችስተር ክለቦች ከተሳካላቸው አንድ አማካይ ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው AS አስነብቧል።እንደ መረጃው ከሆነ ማድሪዶች ፖል ፖግባን አልያም ፊል ፎደንን ለመውሰድ ትልቅ ፍላጎት አላቸው። 





ኤሲ ሚላኖች በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ግብ ጠባቂያቸው ጂአሉጂ ዶናሮማ በሚላን እንደሚቆይ መተማመናቸውን Corriere della Sera አስነብቧል።እስካሁን ኮንትራት ለሚላን ባያራዝምም በቅርብ ጊዜያት አዲስ ኮንትራት እንደሚፈርም ሚላኖች ተማምነዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...