አርሰናል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማዘዋወር ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች ዋነኛው ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ አማካይ ኢስኮ ነው።መድፈኞቹ ተጫዋቹን መውሰድ የሚፈልጉት በውሰት ሲሆን ሲቪያም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(AS, via Metro)
ኔዘርላንዳዊው አማካይ ጆርጂንሆ ዋይናልደም በሊቨርፑል የሚኖረውን ቆይታ በዚህ ሳምንት እንደሚወስን ታውቋል።በባርሴሎና በጥብቅ የሚፈልገው አማካዩ በአንፊልድ ያለው ኮንትራት ሰኔ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
(Sky Sports)
ማንቸስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን ምትሀተኛ ሊዮኔል ሜሲ በ2021 ለማዘዋወር ተስፋን ሰንቋል።ሜሲ በቅርቡ አንድ ቀን በሜጀር ሊግ ሶከር እንደሚጫወት ተስፋ እንዳለው መናገሩ ይታወሳል።
(Telegraph)
አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ፓሪሰን ዤርመንን ከተረከበ በኋላ ከቀድሞው ክለቡ ቶተንሀም በርካታ ተጨዋቾችን ለማስፈረም አቅዷል።ሁጎ ሎሪስ እና ዴሊ ዓሊ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው።
(Eurosport)
ጥር ላይ ውሉ የሚጠናቀቀውን ስፔናዊውን የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ ዲዬጎ ኮስታን ለማዘዋወር ዎልቭስ እየሞከረ ነው።ዎልቭስ ራውል ሂሜኔስን በጉዳት ማጣቱ ይታወሳል።
(Times - subscription required)
ሆላንዳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ፎዙ ሜንሳህ በማርሴይ እና ሀርታ በርሊን እየተፈለገ ነው።
(Football Insider)
ቶተንሀም የሌብዚኹን ኦስትሪያዊ አማካይ ማርሴል ሳቢዘር በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ይፈልጋል።
(Evening Standard)
ሊቨርፑል የኢንተር ሚላኑን ስሎቬኒያዊ ተከላካይ ሚላን ስክሪኒያር ለማዘዋወር የነበረውን ሙከራ አቁሟል።£54ሚ. በመጠየቁ ምክንያት።
(Calciomercato - in Italian)
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና ዩቬንትስ አሰልጣኝ ፋቢዮ ካፔሎ ፓውሎ ዲባላን በሀሪ ኬን ብቻ መቀየር እንደሚያዋጣ ተናግረዋል።
(Gazzetta dello Sport)
No comments:
Post a Comment