Saturday, December 26, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

    አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ 


ቼልሲዎች በብዙ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘውን የቦሩሲያ ዶርትመንዱን ወጣቱን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድን በቀጣይ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ዝግጁ መሆናቸውን Sky Sport Italia አስነብቧል። ተጨዋቹን ከቸልሲ በተጨማሪ በማንችስተር ሲቲም ይፈለጋል። 





ኤቨርተን እና ወልቭስ በስትራስቡርጉ ተከላካይ መሀመድ ሲማካን ዝውውር ላይ ተፋጠዋል።የ20 አመቱን ተከላካይ ለማስፈረም ሁለቱም ክለቦች £20m እንደሚያስወጣቸው Tuttomercatoweb አስነብቧል። ስትራስቡርጎች ተጨዋቹን ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው። 





ሊድስ ዩናይትዶች ስፔናዊውን የዎልቭስ የመስመር አጥቂ አዳማ ትራኦሬን በጥር የዝውውር ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።ወልቭሶች ተጨዋቹን በቀላሉ አሳልፈው እንደማይሰጡ ቢታወቅም ሊድሶች ግን ልጁን ለመውሰድ ካሁኑ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን 90Min አስነብቧል። 





ትናንት አሰልጣኛቸውን ያሰናበቱት ፒኤስጂዎች የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር አሁን ላይ ፊታቸውን ወደ ቸልሲው ጀርመናዊ ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር ማዞራቸውን Le Parisien አስነብቧል። ተጨዋቹ በባርሴሎና ጁቬንቱስም ይፈለጋል። 





ኢንተር ሚላኖች የዩዲኔዚውን የ26 አመት አማካይ ሮድሪጎ ዲፖልን በጥር የዝውውር መስኮት እንደሚያስፈርሙት መተማመናቸውን Calcio Mercato ሲያስነብብ ሊድሶችም ተጨዋቹን ይፈልጉታል። 



ባርሴሎናዎች በጥር የዝውውር መስኮት ከሽኩድራ ሙስጣፊ እና ከአንቶኒዮ ሩዲገር አንዳቸውን ወደ ካምፕኑ ለማምጣት መዘጋጀታቸውን SPORT አስነብቧል።ነገር ግን ሩዲገርን ከባርሴሎና በላይ ፒኤስጂዎች ልጁን የማግኘት ሰፊ እድል አላቸው። 




 

አትሌቲኮ ማድሪዶች የኬራን ትሪፒየር የ10 ሳምንት ቅጣት ሚፀናባቸው ከሆነ በቀኝ መስመር ተከላካይ ሌላ ተጨዋች ለማስፈረም እንደሚፈልጉ The Sun አስነብቧል።የአትሌቲኮዎች ቀዳሚ ምርጫ ደሞ ሌላኛው እንግሊዛዊ የአርሰናል የቀኝ መስመር ተከላካይ ሚትላንድ ናይልስ ነው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...