Thursday, December 24, 2020

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

 የሀገር ውስጥ 

ዛሬ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከተማ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ጅማ አባ ጅፋርን 4ለ1 አሸንፏል።






የውጭ


ቼልሲ ኖርዌጅያኑን አጥቂ አርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር የሚደረገውን ፉክክር ተቀላቅሏል።ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲ ከሁሉም ፈላጊዎች በተሻለ የማዘዋወር ዕድል እንዳለው እየተነገረ ነው።

(90 min)







የኤሪሊንግ ሀላንድ ወኪል ከሆነው ሚኖ ራዮላ ጋር ግጭት ወስጥ ያለ የሚመስለው ማንቸስተር ዩናይትድ ፊቱን ወደ ኤቨርተኑ እንግሊዛዊ አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት ሊውን አዙሯል ።

(Mirror)






ፓሪሰን ዤርመን የተከላካይ መስመሩን ለማጠናከር ጀርመናዊው የቼልሲ ተከላካይ ሩዲገር ለማዘዋወር እየሰራ ነው።

(Le Parisien - in French & subscription

required)






ሊቨርፑል የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።አርጀንቲናዊው ክለብ አልባ ኤዝኩዌል ጋራይም የዠርገን ክሎፕ አይን ያረፈበት ተጨዋች ነው።

(Todofichajes - in Spanish)






ቀውስ ላይ ያለው አርሰናል የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ቪኒሺየስ ጁኒየር በውሰት ለማዘዋወር እየሰራ ነው።አርቴታ ከሎስብላንኮዎቹ ኢስኮንም የሚፈልግ ቢሆንም ስፔናዊው አማካይ ግን ዩቬንትስን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

(Daily Star)






ባርሴሎና ኮንትራቱ በአመቱ መጨረሻ የሚጠናቀቀውን ጀርመናዊውን ተከላካይ ሽኾድራን ሙስጣፊ ከአርሰናል በነፃ ማዘዋወር ይፈልጋል ።

(SPOX via 90 min)






ማንቸስተር ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የመስመር አጥቂ ሄሴ ሊንጋርድ ውል እስከ  2022 ድረስ ሊያራዝምለት ነው።

(Mail)






በPSV የሚገኘው ማሪዮ ጎትዘ በአመቱ መጨረሻ ወደ ባየርን ሙኒክ የመመለስ ዕድል እንዳለው ተናገረ።

(Bild - in German)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...