የሀገር ውስጥ ዜናዎች
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንን ቀነኒሳ በቀለ አሸነፈ፡፡ቀነኒሳ 2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ 41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው፡፡ቀነኒሳ የአለም የማራቶን ሪከርድን ለማሻሻል 2 ሰከንድ ብቻ እንደዘገየ ነው የተነገረው፡፡በውድድሩ ብርሃኑ ለገሰ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ ሲሳይ ለማ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡(FBC)
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሴቶች የበርሊን ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።ውድድሩን አሸቴ በከሪ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ 14 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ አንደኛ ሆና አጠናቃለች።ማሬ ዲባባ ደግሞ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ 22 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
(FBC)
የውጭ ሀገር ዜናዎች
የቶተንሀም ተጨዋቾች አሰልጣኛቸው ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ በቅርቡ እንደሚሰናበት እንደሚያምኑ ተነግሯል።አርጀንቲናዊው ድንቅ አሰልጣኝ ኦሊ ጉናር ሶልሻየርን በመተካት ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ እንደሚያቀና በስፋት እየተዘገበ ነው።(Sun on Sunday)
ፖቼቲንሆ ቶተንሃምን ይለቃል የሚለው ዜና ሚዛን እየደፋ መምጣቱን ተከትሎ ስፐርስ አርጀንቲናዊውን ሰው የሚተካለትን እየፈለገ ይገኛል።የሰሜን ለንደኑ ክለብ የመጀመሪያ ምርጫም የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት መሆኑ ታውቋል።
(Star Sunday)
በሪያል ማድሪድ ቤት የውጤት ቀውስ መከሰቱን ተከትሎ ፕሬዝደንቱ ፍሎረንቲኖ ፒሬዝ የቀድሞውን የቼልሲ እና የማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም የራሱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ የነበረውን ጆዜ ሞሪንሆን ወደ ሳንቲያጎ ቤርናቢዮ ለመመለስ እየሰሩ ነው።ሶስት ጊዜ በተከታታይ ሻምፒዮንስ ሊግን አሳክቶ በድንገት ከክለቡ በገዛ ፍቃዱ ከወጣ በኋላ በድጋሚ የተመለሰው ዚነዲን ዚዳን በስፔኑ ሐያል ክለብ አመቱ የሰመረ አልሆነለትም።
( Sunday Times)
ሊቨርፑል የ22 አመቱን ብራዚላዊ የአያክስ አጥቂ ዳቪድ ኒሬስ ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Calciomercato)
ለረዥም አመታት የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን የመሩት ጆዋኪም ሎ ከሀላፊነታቸው ሲሰናበቱ መንበረ ስልጣኑን የጌጌም ፕሬሲንጉ አቀንቃኝ የርገን ክሎፕ ይረከቡታል ተብሎ ይጠበቃል።
(Sunday Mirror)
ዌስት ሀም እንግሊዛዊው የ20 አመት አማካይ ዴክላን ሪስ መሸ'ጫ ዋጋው £100M መሆኑን አሳውቋል።የለንደኑ ክለብ ይህንን ያለው በተለይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቹን የማዘዋወር ፍላጎት ማየሉን ተከትሎ ነው።
(Sunday Express)
ባርሴሎና በአመቱ መጨረሻ በስታንፎርድ ብሪጅ ያለው ኮንትራት የሚያበቃውን ብራዚላዊውን አጥቂ ዊሊያን ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።የካታላኑ ክለብ የ 31 አመቱ ተጨዋች የረዥም ጊዜ ፈላጊ መሆኑ ይታወሳል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በጥር ወር በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ክለቡ ምንም አይነት ተጨዋች እንደማያስፈርም ተናግሯል።ስፔናዊው የቲኪ ታካ አቀንቃኝ ለዚህ ያቀረበው ምክንያት 'ገንዘብ ስለሌለን' የሚል መሆኑ ብዙዎችን አስፈግጓል።
(Sky Sports)
No comments:
Post a Comment