Sunday, July 28, 2019

የእሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ


ዩናይትድ ፖርቹጋላዊውን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል ተጨዋቹ ለህክምና ምርመራ ወደ እንግሊዝ ሊያመራ እንደሆነ ዩናይትድ ለልጁ £63m ያወጣሉ ተብሏል




ዎልቭሶች የፓትሪክ ኩትሮኔን ዝውውር ከኤሲሚላን ለመጨረስ ተቃርበዋል ከቡድኑ ጋር አሜሪካ ለቅድመ ውድድር ቢያመራም አሁን ወደ ጣሊያን ተመልሧል ስለዚህ ወደ ወልቭስ ሊመጣ መቃረቡ ተነግሯል




የቦካ ጁኒየርስ ክርስቲያን ፓቮን ሪከርድ በሆነ ዋጋ ወደ ሎሳንጀለስ ለመሄድ ተቃርቧል ከዚህ ቀደም በባርሴሎና በአርሰናል ሲፈለግ እንደነበረ ይታወሳል በመጨረሻም ግን ሊያመራ ተቃርቧል




ጁቬንቱስ ማንችስተር ዩናይትድ ማንሲቲ ሊያስፈርሙኝ ፈልገውኝ ነበር ነገር ግን ወደ ኢንተር ሚላን መሄድን መርጫለው የሚል አስተያየቱን ዲያጎ ጎዲን ተናግሯል




ፓብሎ ዲባላ በጁቬንቱስ መቆየት ይፈልጋል እንግዲ ሳሪ ሊጫወት በሚፈልግበት አጨዋወት ምቹ ነው ለዛም ነው በጁቬ ቆይቶ በቦታው ታግሎ ለመቆየት የወሰነው ተብሏል




አርሰናል ኤቨርተን ሱዋሬዝን የማግኘት እድሉ ሰፍቷል የኒኮላስ ፔፔን ዝውውር የጨረሱት አርሰናሎች አሁን ደሞ ፊታቸውን ወደ ኮፓ አሜሪካው ኮከብ ተጨዋች ኤቨርተን ሱዋሬዝ አዙረዋል ልጁም በግሉ ወደ አርሰናል ማምራት ይፈልጋል





ፖል ፖግባ ወደ ማድሪድ የመሄድ እድሉ ከፍተኛ ሆኗል የ26 አመቱን ፖግባን ማግኘታቸውን እርግጠኛ ሆነዋል ዩናይትድም ልጁ ሚለቅ ከሆነ ዝውውሩ በቶሎ እንዲጠናቀቅላቸው ይልጋሉ ዩናይትዶች ለተጨዋቹ 150ሚዩ ነው የሚፈልጉት




የቀድሞ የቸልሲ ኮከብ ኦስካር ወደ አውሮፓ ተመልሶ መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል ጣሊያን ደሞ ምርጫዬ ናት ብሏል ከኤሲሚላን እና ከኢንተርሚላንም ጥያቄ እንዳቀረቡለትም ተናግሯል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...