Sunday, July 28, 2019

የእሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ


ኤቨርተኖች የጁቬንትሱን አጥቂ ሞይስ ኪንን ለማስፈረም ንግግር ጀምረዋል ጁቬዎች ለተጫዋቹ 40ሚ.ዩሮ እንዲቀርብላቸው የጠየቁ ሲሆን ስምምነቱ ላይ ተጫዋቹን መልሶ የመግዛት መብት እንዲኖራቸውም ይፈልጋሉ




ሀሪ ማጓየር ክለቡን ለመልቀቅ እንዳልተቃረበ አሰልጣኙ ብሬንዳን ሮጀርስ ተናገረ ከስቶክ ጋር በነበረው የዝግጅት ጨዋታ ላይ ሙሉ 90 ደቂቃ የተጫወተ ሲሆን በየትኛውም የዝውውር ዜና እና ወሬ አይረበሽም ብለዋል




ሮይ ሆድሰን ስለ ዘሀ ቆይታ ምንም እንደማያውቁ ተናገሩ ስሙ በሰፊው ከአርሰእና ኤቨርተን ጋር እየተነሳ የሚገኘው ተጫዋቻቸው መጨረሻው ምን እንደሚሆን መገመት ይከብደኛል ብለዋል




የላዚዮው አሰልጣኝ ኢንዛጊ አማካዩ ሚሊንኮቪች ሳቪች ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተናገረ እሱ ተጫዋቹ እንዲቆይ ቢፈልግም ማንቺስተርና ላዚዮ በተጫዋቹ 90 ሚ.ዩሮ የዝውውር ዋጋ ለመስማማት እንደተቃረቡ ተዘግቧል




ዳኒ አልቬስ በቅርቡ አዲስ ክለብ እንደሚቀላቀል ተዘገበ በዝውውር መስኮቱ ስሙ አርሰናልን ጨምሮ ከተለያዩ ክለቦች ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የ 36 አመቱ ተጫዋች ከፒኤስጂ ከተለያየ ቡሀላ ክለብ እንደሌለው ይታወቃል




ሚኪ ባትሽዋይ በቼልሲ ቤት ቆይቶ ከጂሩድና ታሚ አብራሃም ጋር ለቦታው እንደሚፎካከር ተናገረ ቼልሲ በዚህ የዝውውር መስኮት በተጣለበት እገዳ ምክንያት እንደማይሳተፍ ይታወቃል




ቶተንሀሞች ለዲባላ ያቀረቡት £50m በጁቬንቱስ ውድቅ ተደረገባቸው አርጀንቲናዊው አጥቂ በፖቼቲኖ በጥብቅ እየተፈለገ ሚገኝ ሲሆን ቶተንሀም በድጋሚ የዝውውር ዋጋውን አሻሽለው ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል





ራጃ ኒያንጎላን ወደ ቀድሞ ክለቡ ካግሊያሪ መመለስ ይፈልጋል የ31 አመቱ ቤልጂየማዊ በኢንተር ሚላን የዘንድሮ እቅድ ውስጥ እንደሌለ ተነግሮታል




ጋሬዝ ቤል ወደ ቻይና ለመዘዋወር ቢቃረብም ቤተሰቦቹ ግን እዛው ስፔን እንደሚቆዩ ተዘገበ ዌልሳዊው ተጫዋች በቻይና በሳምንት 1 ሚ.ፓ እየተከፈለው ለሶስት አመት ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል




ሮሜሉ ሉካኩ የመሸጫ ዋጋው እንዲቀንስ ሶልሻ ጠየቀ ከክለቡ ለመውጣት በር ላይ የሚገኘው ቤልጄማዊ አጥቂ ዩናይትዶች ዋጋውን ቀንሰው በቶሎ እንዲለቁት ፈልጓል የተጫዋቹ ፈላጊዎች ኢንተርና ጁቬ ዩናይትድ ሚጠይቀውን £80m ለመክፈል ፈቃደኛ አይደሉም




ሪያል ማድሪድ ለፖል ፖግባ 150 ሚ.ፓ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል ጋሬዝ ቤልን ወደ ቻይና ለመሸኘት የተቃረበው ማድሪድ ፈረንሳያዊውን አማካይ ለማምጣት ቆርጠዋል ፖግባ ማድሪድን የሚቀላቀል ከሆነ በክረምቱ ወደ ማድሪድ የመጣ 5ኛው ተጨዋች ይሆናል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...