የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ - ኢብራሒም መሐመድ
ፒኤስጂዎች የ23 አመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ አብዱ ዲያሎን ከቦሩሲያ ዶርትመንድ ማስፈረሙ ተረጋግጧል ለልጁም ለዶርትመንድ 20ሚፓ ያወጣ ሲሆን በፒኤስጂም አምስት አመት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል
በቅርቡ ራፋ ቤኒቴዝን ያሰናበቱት ኒውካስትል ዩናይትዶች በፕሪሚየር ሊጉ በማሰልጠን ብዙ ልምድ ያላቸውን ስቲቭ ብሩስን ከሰአታት በፊት አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል
አርሰናሎች የሪያል ማድሪዱን ዳኒ ሴቫዮስን በውሰት ለማስፈረም ከማድሪድ ጋር ንግግር እያደረጉ ነው በቀጣይ ቀናትም ጥያቄያቸው ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ በአንድ አመት የውሰት ውል ወደ ኢምሬት እንደሚመጣ ተነግሯል
የሌስተሩ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ ለሀሪ ማጉዋየር የመጣ እሱን የማይመጥን ውል ሁለት ጊዜ ውድቅ እንዳደረጉ ተገለፀ።
አርሰናል የ33አመቱን ፈረንሳዊ ተከላካይ ኮሼልኒ ለመሸጥ ፍቃደኛ መሆኑ ስካይ ስፖርት ዘግቧል ልጁ ወደ ትውልድ ሀገር ተመልሶ መጫወት ይፈልጋል ከአርሰናል ጋር የአንድ አመት ውል ቢቀረውም አርሰናልን በነፃ ነው መልቀቅ ሚፈልገው ለልጁም ተገቢውን ክፍያ ካገኙ እንደሚለቁት ታውቋል የፈረንሳዩ ሊዮን እና ማርሴይ የልጁ ፈላጊ ክለቦች ናቸው
ኤቨርተኖች አዴሞላ ሉክማንን ለአርቢ ሌብዢግ በ 22.5 ሚሊየን ፓውንድ ለመሸጥ ተስማምተዋል ዝውውሩ በ 24 ሰዓት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል
የጀርመኑ አርቢ ሌብዢክ የፓሪሰን ዤርሜኑን ክሪስቶፈር ንኩኩን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል በጀርመኑም ክለብ አምስት አመት የሚያቆየውን ውል ይፈርማል
የፈረንሳዩ ክለብ ሬንስ የሳውዛንብተኑን የመስመር ተጨዋች ሱፍያን ቦፉልን ለመስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ለዝውውሩ እስከ €10m የሚከፍሉ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ዝውውሩ እንደሚጠናቀቅ ተነግሯል
አስቶን ቪላዎች ቤልጂየማዊውን የ ስቴድ ሬይምስ የመሀል ተከላካይ ግልፅ ባልተደረገ ሂሳብ ማዘዋወራቸውን ይፋ አድርገዋል
ሮማዎች የፊዮሬንቲናውን ጆርዳን ቬሬታውትን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል ሮማ ለልጁ €17 + €2ቦነስ የሚከፍሉ ይሆናል ዝውውሩንም ለመጨረስ ትናንት የመጨረሻ ድርድር ማድረጋቸው ታውቋል
No comments:
Post a Comment