Tuesday, July 16, 2019

የረቡዕ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

የረቡዕ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች


አቅራቢ - ኢብራሒም መሐመድ

እንግሊዛዊው የቶተንሀም  የቀኝ መስመር ተከላካይ ቴራን ትሪፒየር ወደ ስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ለማቅናት ከጫፍ ደርሷል ቶተንሀም እና አትሌቲኮዎች በ£20m የተስማሙ ሲሆን ሜዲካሉንም ለማድረግ ወደ ስፔን አምርቷል በ24ሰአት ውስጥም ዝውውሩም ይፋ ይሆናል



አርሰናል ዳኒ አልቬስን ሊያስፈርም ከጫፍ ስለመድረሱ ተነግሩዋል ተጫዋቾቹም ዳኒ ሴባዮስ እና ዳኒ አልቬስ ናቸው የቀኝ መስመሩ ተከላካይ አልቬስ ፓሪስን ከለቀቀ ቡሀላ ክለብ የለውም ማን ሲቲ ቶተንሀም እና አርሰናል ፈላጊዎቹ ሲሆኑ ነገር ግን አርሰናል በሳምንት 200.000ሺፓ ሊከፍለው እና ወደ ኢምሬት ሊያመጡት ፍላጎት አላቸው




ጁቬንቱሶች ወጣቱን ሞይሴ ኪንን ለመልቀቅ አስበዋል ፈላጊ ክለቡ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች ንግግር እያደረጉ እንደሆነ ተሰምቷል ዶርትመንዶች 35ሚዩ እና ጁቬንቱሶች ይህንን ተጨዋች ከፈለገ እና መልሶ ለመግዛት ካሰቡ ቅድሚያ ለመስጠት ተስማምተዋል ተብሏል




ባርሴሎናዎች ማርክ ኩኩሬላን ከአይባር መልሶ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል የ20አመቱ የግራ መስመር ተከላካይ አምና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ነበር በ2ሚዩ የተዘዋወረው ነገር ግን ባርሴሎና በሽያጭ ውሉ ላይ ባርሳ በእጥፍ ዋጋ የመግዛት መብቱን ተጠቅሙ ወጣቱን ተከላካይ አስፈርሞታል




ፍራንክ ላምፓርድ ካሉም ሆድሰን ኦዶይ በቼልሲ እንዲቆይ እንደሚፈልግ ተናገረ ባየርን ሙኒክ የልጁ ፈላጊ መሆኑ ይታወቃል የሙኒኮችም ገፋ ያለ ጥያቄ ልጁ ወደ ሙኒክ ሄዶ የመጫወት ፍላጎቱን ከፍ እንዲል አርጎ ነበር ላምፓርድ ግን እንደ ኦዶይ ያሉ ወጣት እና ድንቅ ታለንት ያላቸው ተጨዋቾች በክለባቸው እንዲቆዩ እና አዲስ ውል እንዲፈርሙ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል




ፒኤስጂዎች ኔይማርን ከገዙበት ዋጋ በታች እንደማይሸጡት ስፖርቲትግ ዳይሬክተሩ ሊዮናርዶ አሳውቀዋል 2017 ላይ በ £197m ያስፈረሙት የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና ልጁን ማዘዋወር ይፈልጋሉ ግን የሸጡበትን ዋጋ መልሰው መግዛት የከበዳቸው ሚመስሉት ባርሳዎች ኩቲንሆን ወይም ዴምቤሌን + 40ሚዩ ቢያቀርቡም ፒኤስጂዎች የሸጥንበትን ንፁህ ገንዘቡን ነው የምንፈልገው በሚል ኔማር ላይ 220ሚዩ መሸጫ ዋጋ ለጥፈውበታል





ቶተንሀሞች ጋሪዝ ቤልን በድጋሚ ወደ እንግሊዝ ለማምጣት ከማድሪድ ጋር ድርድር ጀምረዋል ከ50 እስከ 60ዩሮ ለመክፈል ፍቃደኛ ነው ነገር ግን በማድሪድ የሚከፈለውን ከፍተኛ ደሞዝ እንደማይከፍለው ተረጋግጧል 17ሚዩ በማድሪድ እየተከፈለው ይገኛል ነገር ግን አሁንም ወኪሉ ይህንን ዜና አስተባብሏል





ማቲያስ ዴሊት ወደ ጁቬንቱስ ለማምራት ትናንት ጣሊያን ገብቷል ዛሬ የጤንነት ምርመራውን ያደርጋል በጁቬንቱስ ከሮናልዶ ቀጥሎ ከፍተኛ ተከፋይ ይሆናል ጁቬዎች ለልጁ £63m ወጪ አድርገዋል የውል ማፍረሻው £135m ሲሆን ግን በየአመቱ £13.5m እየጨመረ እንደሚሄድ ታውቋል



ማን.ሲቲዎች ማንጋላን በነፃ ሊለቁት ነው ለዚም በክለቡ ማረጋገጫ እንደተሰጠው ታውቋል በቅድመ ውድድር ዝግጅት በክለቡ ሪፖርት አድርጎ ነበር ግን ሲቲዎች ወደ ቻይና ባደረጉት ጉዞ ልጁን አላካተቱትም



ኤቨርተኖች ማርዮ ማንዙኪችን ከጁቬንቱስ ለማስፈረም ይፈልጋሉ  15ሚዩ ደሞ ለጁቬንቱስ ለመክፈል ይፈልጋሉ ነገር ግን ጁቬንቱስ ላይቀበል ይችላል የሚል መረጃዎች ከጣሊያን መውጣት ጀምረዋል ገንዘቡ ያንሳል ነገር ግን በገንዘብ ጉዳይ ከተስማሙ ልጁን መውሰድ እንደሚችሉ ታውቋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...