አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ቼልሲ የቀድሞ ኮከቡን ፍራንክ ላምፓርድ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በአሰልጣኝነት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።ሰማያዊዎቹ ለምንጊዜም የክለባቸው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ የሶስት አመት ኮንትራትም ይሰጡታል ተብሎ ይታሰባል።ላምፓርድ በደርቢ ካውንቲ ያሳየው አቋም በሮማን አብራሃምሞቪች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።
( Standard )
ማን ዩናይትድ ዋን ቢሳካን ለማዘዋወር በ£55ሚ. ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱ ተነግሯል።የ21 አመቱ እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል በኦሊጉናር ሶልሻየር በጥብቅ የሚፈለግ ሲሆን የአንቶኒዮ ቫሌንሲያ የረዥም ጊዜ ተተኪ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።
(Record )
የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኔይማር ወደ ባርሴሎና ይመለሳል የሚለው ዜና ዛሬም በስፋት እየተነሳ ያለ መረጃ ነው።ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ወደ ካላታኑ ክለብ መመለስ እንደሚፈልግ ለፓሪሱ ክለብ ፕሬዝዳንት ናስር አል-ኻላፊ እንደነገራቸው መነገሩ ይታሰባል።
( Sport )
ሌላ ኔይማርን በተመለከተ የወጣው ዜና ደግሞ ሪያል ማድሪድ ተጨዋቹን ለማዘዋወር እየሰራ ነው የሚል ነው።የካታላኑ ጋዜጣ ሙንዶ ዲፖርትሪቮ እንደዘገበው ሎስብላንኮዎቹ ለፓሪሱ ክለብ £115ሚ. እና ጋሬዝ ቤልን ወይም ሀሜስ ሮድሪጌዝን አቅርበዋል።ፒ.ኤስ.ጂ ከሁለቱ የስፔን ክለቦች አንዱን የመምረጥ ግዴታ ውስጥ የገባ ይመስላል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
ባየርን ሙኒክ በማንቸስተር ሲቲ በጥብቅ እየተፈለገ የሚገኘውን ስፔናዊውን የ22 አመት አማካይ ሮድሪ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ፔፕ ጋርዲዮላ የተጨዋቹ ቀንደኛ ፈላጊ ነው።
( AS - in Spanish)
ከአመት በፊት በ£50ሚ. ቼልሲን የተቀላቀለው ጆርጊንሆ የማውሪዚዮ ሳሪን መሰናበት ተከትሎ አብሯቸው ወደ ቱሪን ይጓዛል ተብሏል።ጣሊያናዊው አሰልጣኝ በጁቬንትስ ስር ተጨዋቹን ይፈልጉታል።
(Mirror )
ኢንተር ሚላን እና አትሌቲኮ ማድሪድ የሳውዝሀምተኑን እንግሊዛዊ የ29 አመት ፉል ባክ ሪያን በርትናንድ ለመዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Mail)
ኦሊጉናር ሾልሻየር ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ እንዲያስፈርምለት ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች አንዱ ዌልሳዊው የበርንማውዝ የ21 አመት አማካይ ዳቪድ ብሮክስ አንዱ ነው።
(Sun)
ትናንት በኮፓ አሜሪካ በምድብ ሁለት በተደረገው ጨዋታ አርጀንቲና ከ ፓራጓይ ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።በጨዋታው የፓራጓዩ ኢቫን ፔሪስ በእጁ የነካው ኳስ በVAR አማካይነት ወደ ፍፁም ቅጣት ምትነት ተለውጦ ሜሲ በ57ተኛው ደቂቃ አስቆጥሮታል።
ሪቻርድ ሳንቼዝ ደግሞ በ37ተኛው ደቂቃ የፓራጓይን ግብ በስሙ ያስመዘገበው ተጨዋች ነው።ፓራጓይ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ የነበር ቢሆንም ዴርሊስ ጎንዛሌዝ የመታውን ኳስ ፍራንሶ አርማኒ መልሷታል።ከሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘችው አርጀንቲና ከምድቡ ለማለፍ እሁድ ተጋባዧን ሀገር ኳታር ማሸነፍ የግድ እና የግዷ ሆኗል።ማሸነፍ ብቻ ግን አያሳልፋትም ፥ ምክንያቱም ፓራጓይ በቀጣዩ ጨዋታ ካሸነፈች የአርጀንቲና ከምድቡ ማለፍ ህልም ሆኖ ይቀራል።
(The Guardian)
አርሰናል በዚህ የዝውውር መስኮት ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች አንዱ ስኮትላንዳዊው የ22 አመቱ የሴልቲክ ፉልባክ ኬረን ቴርኒ አንዱ ነው።
(Mail)
ጁቬንትስ በቀድሞው ተጨዋቹ ፖል ፖግባ ጉዳይ ሪያል ማድሪድን እንደሚረታ ተስፋ አድርጓል።ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ከኦልድ ትራፎርድ በዚህ የዝውውር መስኮት መውጣቱ አይቀሬ መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ነው።
(Mirror )
ምርጥ አሸራራብ ቀጥሉበት
ReplyDelete