ከሰዓት የወጡ ዜናዎች
°ስፔናዊው የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ኢብራሂም ዲያዝ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ሪያል ማድሪድ ለመዘዋወር Informal በሆነ መልኩ መስማማቱን ጎል አስነብቧል ።የ19 አመቱ ስፓኒያርድ ተስፈኛ ከሚባሉ ተጨዋቾች አንዱ ነው።
(Goal)
°የቀድሞው የኤሲ ሚላን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማሲሚሊያኖ ሪቤሊ ባሳለፍነው አመት ክለባቸው በአሁን ሰዓት ጁቬንትስ በመጫወት ላይ ያለውን ፖርቹጋላዊ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለማስፈረም ጥረት አድርጎ እንደነበር ተናገሩ።ሆኖም በወቅቱ የነበሩት የክለቡ ባለሀብቶች ጉዳዩን እንዳልተቀበሏቸው ተናግረዋል ።
(Sportitalia via Mail)
°ኤሲ ሚላን ስፔናዊውን የቼልሲ አማካይ ሴስክ ፋብሪጋዝ ለማዘዋወር ንግግር መጀመሩ ታውቋል።የ31 አመቱ የቀድሞው መድፈኛ በስታንፎርድ ብሪጅ የእግር ኳስ ህይወቱ እያከተመ ይመስላል ። (Calciomercato)
°ማንቸስተር ሲቲ የቤኔፊካውን ድንቅ የ17 አመት ታዳጊ አማካይ ቲያጎ ዳንታስ የማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት አለው ተባለ።ፔፕ ጋርዲዮላ የልጁ አድናቂም ነው።
(Record, via Manchester Evening News)
°አርሰናል እና ቶተንሀም ጀርመናዊውን የሆፈንየም አማካይ ናዲየም አሚሪ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ እንዳሉ የጀርመኑ ተነባቢ ጋዜጣ ቢልድ ዘግቧል። ቢልድ በዘገባው እንዳተተው ከሆነ የ22 አመቱ አማካይ ምንም እንኳን በዘንድሮው አመት በጉዳት ምክንያት መጫወት ያልቻለ ቢሆንም ሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች ግን የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸዉ ።
(Bild)
°ማንቸስተር ዩናይትድ የ24 አመቱን አይቮሪ ኮስታዊ ተከላካይ ኤሪክ ቤሊ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊሸጠው ይችላል ።
(Manchester Evening
News)
°የሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ፊሊደልፊያ ዩኒየን የቀድሞውን የማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል አጥቂ ማርዮ ባላቶሊ ለማዘዋወር እንቅስቃሴ ጀምሯል ።የ28 አመቱ አወዛጋቢ ሰው በአሁኑ ሰዓት በፈረንሳይ ለኒስ በመጫወት ላይ ይገኛል ።
(Goal)
ጠዋት የወጡ ዜናዎች
¤ባርሴሎና የቼልሲውን የመሀል ተከላካይ አንድሬስ ክርስቲያንሰን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ጥረት ሊያደርግ ይችላል ።ካታላን ዘመም የሆነው ጋዜጣ SPORT እንዳተተው ብሉግራናዎቹ ይህንን የሚያደርጉት ሳሙኤል ኡምቲቲን ያጋጠመው የጉልበት ጉዳት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ከሆነ የሱን ቦታ ለመሸፈን ነው።
ዴንማርካዊው ተከላካይ ማውሩዚዮ ሳሪ ከሲ ይልቅ ለአንቶኒ ሩዲገር እና ለዴቪድ ሊወዝ የቅድሚያ ተሰላፊነት እየሰጡ በመሆኑ ደስተኛ አይደለም በሰማያዊዎቹ ቤት።
¤በሻምፒዮንስ ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ወደ ማርሴ ተጉዞ 2አቻ በተለያየበት ጨዋታ ለፈረንሳዩ ክለብ አስደናቂ አቋም ያሳየው ማግዙዌል ኮርኔት በፔፕ ጋርዲዮላ አይን ውስጥ መግባቱን calciomercato አስነበበ።
በማክሰኞ ምሽቱ ጨዋታ ሁለት ግብ ውሃ ሰማያዊዎቹ ላይ ያሳረፈው ኮርኔት በማርሴ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን ማንቸስተር ሲቲ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ነው ለማዘዋወር የሚፈልገው።
¤የፖል ፖግባ ወኪል የሆነው አነጋጋሪው ሚኖ ራዮላ ለደንበኛቸው ክለብ እያፈላለገ መሆኑን Tuttosport አስነብቧል ።
የጣሊያኑ ጋዜጣ እንዳተተው ፈረንሳዊው ኮከብ ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር ማንቸስተር ዩናይትድን ለቆ ወደ ሌላ ክለብ የሚሄድበትን መንገድ እየፈለጉ ነው።
ፖግባ እና ሞሪንሆ ቅራኔ ወስጥ ከገቡ የሰነባበቱ ሲሆን ጋዜጣው እንዳለው ቀያይ ሰይጣኖቹ አሰልጣኙን መርጠዋል ።
¤ባለፉት ሳምንታት የአለም የእግር ኳስ ተመልካቾችን የሳበው የቦካ ጁኒየርስ እና ሪቨር ፕሌት ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናቢዮ ሊደረግ እንደሚችል As አስነብቧል ።
በላቲን አሜሪካው ሻምፒዮና ኮፓ ሊበርታዶሬስ የተገናኙት ሁለቱ የአርጀንቲና ጉምቱ ክለቦች በመጀመሪያው ጨዋታ 2ለ2 ከተለያዩ በኃላ የመልሱ ጨዋታ በነውጥ ምክንያት መደረግ አለመቻሉ ይታወቃል ።
¤የጁቬንትሱ ግብ ጠባቂ ወንቼክ ሼዝኒ ከክለቡ እንደማይለቅ ወኪሉ ተናገረ።ወኪሉ ጆናታን ባርኔት ደንበኛው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ግብ ጠባቂ ያን ኦብላክ ጋር የሚያወዳድር ብቃት እንዳለውም ተናግሯል ።
¤ቶተንሀም በሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈለገውን ኤሪክሰን €250M እንደለጠፈበት የማድሪዱ ጋዜጣ Marca አስነብቧል ።
ስፐርስ ተጫዋቹን የመሸጥ ፍላጎት ፍፁም የሌላት ቢሆንም የፍሎረንቲኖ ፔሬዝ አስተዳደር ገፍቶ ከመጣ ግን በከፍተኛ ዋጋ የመሸጥ ፍላጎት አላት ።
¤በማውሩዚዮ ሳሪ ስር እየባከነ የሚገኘው ካንቴ ሊሸጥ እንደሚችል talksport ዘግቧል። ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ከመጡ ወዲህ በተከላካይ አማካይነት መሰለፍ ያልቻለው ካንቴ አሁን ባለው አስር ቁጥር (ከአጥቂ ጀርባ) ሚና ፍፁም ደስተኛ አይደለም ።ሳሪ ጆርጊንሆን ከዚህ በኃላም የሚመርጡ ከሆነ የፈረንሳዊው ዝምተኛ ተጨዋች የመልቀቅ ዕድል ሰፊ ነው።
¤አርሰናል ዴምቤሌን ማስፈረም እንዳለበት የቀድሞው ኮከብ ሬ ፓውለር ተናግሯል ።በባርሴሎና ቤት በተደጋጋሚ ከአሰልጣኙ ጋር በመጋጨት ላይ ያለውን ፈረንሳዩ ማስፈረም ለአርሰናል እጅግ ጠቃሚ መሆኑንም ተናግሯል ።
የቀድሞው የአርሰናል ሌጀንድ እንዳለው ከሆነ ኡናይ ኤምሬ የልጁን ባህሪ የሚያስተካክሉት ከሆነ ቢያስፈርሙት ጥሩ ነው።
¤ጁቬንትስ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሚሊንኮቪች ምክንያት ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸውን Goal ዘግቧል። የፊዮሬንቲናው ተከላካይ ለረዥም ጊዜ በማንቸስተር ዩናይትድ ሲፈለግ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ ጁቬንትስ ውድድሩን ተቀላቅሏል ።
¤አትሌቲኮ ማድሪድ ቶርገን ሀዛርድን የማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ማርካ አስነብቧል ።የሞንቼግላድባው አማካይ በዘንድሮው የውድድር አመት ከመሀል ሜዳ እየተነሳ ስምንት ግቦችን ማስቆጠርም ችሏል።
ተጨዋቹ በጀርመኑ ክለብ እስከ 2020 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።
No comments:
Post a Comment