Tuesday, December 29, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች

 የሀገር ውስጥ 

ዛሬ በቤትኪንግ የኢትይጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን 3ለ2 ረትቷል።በዚህ ጨዋታ ሙጂብ ቃሲም ሀትሪክ በመስራት በዘንድሮው አመት የመጀመሪያው ተጨዋች ሆኗል።




ከውጭ

አስቶንቪላዎች የ29 አመቱን የኢንተር ሚላን አማካይ ማቲያስ ቬሲኖን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Calcio Mercato አስነብቧል። ኢንተሮች ተጨዋቹን ለመልቀቅ ዝግጁ ሆነዋል ፤  ቬሲኖን በኢንተር የ18 ወራት ኮንትራት ብቻ ይቀረዋል። 





ዲያጎ ኮስታ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለመለያየት ከጫፍ መድረሳቸውን SPORT አስነብቧል። የኮስታ የልቀቁኝ ደብዳቤ በአትሌቲዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል።አትሌቲዎችም በኮስታ ምትክ የናፖሊውን ሚሊክን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። 





አርሰናሎች አይናቸውን የሲቪያው አማካይ ጆን ጆርዳን ላይ ማረጋቸውን The Sun አስነብቧል።አርሰናሎች የ26 አመቱን አማካይ ለማግኘት እስከ £55M እንደሚያስወጣቸው ተነግሯል። 





ኢንተር ሚላኖች በቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ቤልጄማዊውን የሊቨርፑል አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ Corriere Dello Sport አስነብቧል። በቀጣይ ክረምት ላውታሮን ለማጣት ሚገደዱት ኢንተሮች ኦሪጊን ለመተካት ፍላጎት አላቸው። 





ጆዜ ሞሪንሆ ከቀድሞ ኮከባቸው ጋር በድጋሚ በቶተንሀም መስራት እንደሚፈልጉ ተሰምቷል። ጆዜ የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ስፔናዊውን የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስን ማስፈረም እንደሚፈልጉ Evening Standard  አስነብቧል።






የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ሊውስ ሳሃ ቀያይ ሰይጣኖቹ በ2021 ጄደን ሳንቾን እና ጃክ ግሪሊሽን ማስፈረም አለበት ሲል ተናገረ።ዩናይትድ ሳንቾን በተደጋጋሚ ለማስፈረም ሞክሮ እንዳልተሳካለት ይታወሳል።





ባለፈው ሳምንት ከወደ ጣሊያን የወጡ መረጃዎች የሜሱት ኦዚል ወኪሎች ከዩቬንትስ ጋር ሊወያዩ ነው ያሉ ቢሆንም goal.com መረጃው ሀሰት ነው ሲል ዛሬ አውጥቷል።ኦዚል በአመቱ መጨረሻ በኤምሬትስ የሚኖረው ኮንትራት የሚያበቃ ይሆናል።






ሜሲ እና ሱዋሬዝ በጋራ 2022 ላይ የሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለመጫወት እቅድ እንዳላቸው Catalunya Radio አስነብቧል።ሜሲ በካምፕ ኑ እስከ 2021 ሱዋሬዝ ደግሞ በዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ እስከ 2022 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...