አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር(የሪሐና ልጅ)
12.መሐመድ ሳላህ
ክለብ - ሊቨርፑል
አመታዊ ክፍያ - $15 ሚለየን (€13.3 ሚሊየን)
⇒በተከታታይ ለሁለት አመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ የነበረው ሙሐመድ ሳላህ በአጠቃላይ ከሁሉም የስፖርት አይነቶች 99ነኛ ከፍተኛ ተከፋይ ሲሆን ከእግር ኳስ ደግሞ 12ተኛ ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
11.ጋሬዝ ቤል
ክለብ - ሪያል ማድሪድ
አመታዊ ክፍያ - $33 ሚሊየን (€29.2 ሚሊየን)
⇒2013 ላይ ሎስብላንኮዎቹን የተቀላቀለው ዌልሳዊ አጥቂ ከእግር ኳስ ተጨዋቾች አስራ አንደኛ ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
10.አንቶኒዮ ግሬዝማን
ክለብ - አትሌቲኮ ማድሪድ / ባርሴሎና (ሙሉ አመቱ ስለሚታይ ነው)
አመታዊ ክፍያ - ያልተገለፀ
⇒ፈረንሳዊው ኮከብ ግሬዝማን በፎርብስ ጥናት መሰረት አስረኛው ከፍተኛ ተከፋይ እግር ኳስ ተጨዋች ነው።
9.ኦስካር
ክለብ - ሻንጋይ ኤስ.አይ.ፒ.ጂ
አመታዊ ክፍያ - $26.5 ሚሊየን (€23.4 ሚሊየን)
⇒በቼልሲ ቤት በነበረው የአምስት አመት ቆይታ ብዙዎች የሚያውቁት ብራዚላዊው ተጨዋች ባልተገመተ መልኩ ወደ ቻይና 2017 ላይ መጓዙ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከእግር ኳስ ተጨዋቾች ዘጠነኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
8.ሜሱት ኦዚል
ክለብ - አርሰናል
አመታዊ ክፍያ - $24 ሚሊየን (€21.2 ሚሊየን)
⇒2013 ላይ መድፈኞቹን በዘመን ቬንገር የተቀላቀለው በትውልድ ቱርካዊ በዜግነት ጀርመናዊ አማካይ ስምንተኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
7.ኪልያን ምባፔ
ክለብ - ፓሪሰን ዤርመን
አመታዊ ክፍያ - $20 ሚሊየን (€17.7 ሚሊየን)
⇒በ2018ቱ የአለም ዋንጫ ሀገሩ ፈረንሳይ ሻምፒዮን ስትሆን ቁልፍ ተጨዋች ነበር ፥ በውድድሩ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ተብሎም ተሸልሞ ነበር።ከድሉ በኋላ የተሰጠውንም $500,000 ለአንድ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ላይ ለሚሰራ የተራድኦ ድርጅት ለግሶ ነበር።
በፎርብስ መረጃ መሰረት ይህ የ20 አመት ወጣት ሰባተኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
6.አሌክሲስ ሳንቼዝ
ክለብ - ማን ዩናይትድ / ኢንተር ሚላን
አመታዊ ክፍያ - $21.5 ሚሊየን (€19 ሚሊየን)
⇒በማን ዩናይትድ ያልተሳካ ጊዜን አሳልፎ ባለፈው ወር የጣሊያኑን ኢንተር ሚላን በውሰት የተቀላቀለው ቺሊያዊ አጥቂ ስድስተኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው።
5.አንድሬስ ኢኒየስታ
ክለብ - ቪሰል ኮቢ
አመታዊ ክፍያ - $30 ሚሊየን (€26.5 ሚሊየን)
⇒ሀያ ሁለት አመታትን በባርሴሎና ያሳለፈው አለም ላይ ከታዩ ድንቅ አማካዮች አንዱ የሆነው ስፓኒያርዱ አንድሬስ ኢኒየስታ አሁን በሚገኝበት የጃፓን ክለብ የሚከፈለው ክፍያ አምስተኛው ከፍተኛ ተከፋይ አድርጎታል።
4.ፖል ፖግባ
ክለብ - ማን ዩናይትድ
አመታዊ ክፍያ - $20 ሚሊየን (€17.7 ሚሊየን)
⇒አራት አመታትን በጁቬንትስ ካሳለፈ በኋላ ወደ ቀድሞው ክለቡ ማን ዩናይትድ የተመለሰው ፖግባ የአለማችን አራተኛው ከፍተኛ ተከፋይ እግር ኳስ ተጨዋች ነው።
3.ኔይማር
ክለብ - ፓሪሰን ዤርመን
⇒የወቅቱ የአለማችን ትልቁ የዝውውር ሒሳብ የወጣበት ተጨዋች የሆነው ኔይማር ሶስተኛው ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ ተጨዋች ነው።
2.ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ክለብ - ጁቬንትስ
አመታዊ ክፍያ - $64 ሚሊየን (€56.5 ሚሊየን)
⇒ከዘጠኝ አመት የሪያል ማድሪድ ቆይታ በኋላ 2018 ላይ የጣሊያኑን ጁቬንትስ ተቀላቅሏል፡፡በዚህም ክለቡ ጁቬንትስ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 520,000 በስሙ የታተሙ ማሊያዎችን በመሸጥ $60 ሚሊየን (€53 ሚሊየን) አስገብቷል፡፡
ፖርቱጋላዊው ተጨዋች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከፍተኛ ግብ አሰቆጣሪነትን ክብር በስሙ መያዙ ይታወቃል፡፡
1.ሊዮኔል ሜሲ
ክለብ - ባርሴሎና
አመታዊ ክፍያ - $80 ሚሊየን (€70 ሚሊየን)
⇒በባርሴሎና በርካታ ክብሮችን ያሳካው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በዚህ አመት በእግር ኳሱ ቁጥር አንድ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋች ነው፡፡
ሜሲ በካታላኑ ክለብ መሰለፍ ከጀመረበት ከ2004 ጀመሮ 33 ዋንጫዎችን በክለቡ አሳክቷል፡
No comments:
Post a Comment