Monday, November 26, 2018

ኔይማር ጉዳት አጋጠመው

የስፖርት ዜና


ትናንት ለሊት በወዳጅነት ጨዋታ ብራዚል ከ ካሜሮን ሲጫወቱ ኔይማር በጊዜ በጉዳት ጨዋታውን አቋርጦ ወቷል 
❇ከየኛ መረጃ/yegnamereja በAbdulkader Beshir (የሪሀና ልጅ) የቀረበ 
✨✨✨✨✨✨✨ 
✅የፒ.ኤስ.ጂው ኮከብ ኔይማር ትናንት ለሊት ሀገሩ ብራዚል ከ አፍሪካዊቷ ካሜሮን ጋር ባደረገችው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ጉዳት አጋጥሞት በጊዜ ጨዋታውን አቋርጧል ።በMK ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ኔይማር ገና በስምንተኛው ደቂቃ የተጎዳ ሲሆን የኤቨርተኑ ሪቻርለሰን ተክቶት ገብቷል። 
ኔይማር በአራት ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ጨዋታውን ሲያደርግ ጉዳቱን ያስተናገደ ሲሆን ከቀናት በፊት ከዩራጓይ ጋር በነበረው ጨዋታ በእርሱ ግብ ብራዚል 1ለ0 ማሸነፏ ይታወሳል ።የሴሌሳኦዎቹ አሰልጣኝ ቲቴ ተጨዋቹ እየበሰለ መምጣቱን መናገራቸው ይታወሳል ። 
የኔይማር መጎዳት ለፒ.ኤስ.ጂ መጥፎ ዜናም ሆኗል ።የፈረንሳዩ ክለብ ቅዳሜ በሊጉ ቱሉዝን ገጥሞ በቀጣዩ ሳምንት የሞት የሽረት ጨዋታውን ከሊቨርፑል ጋር በሻምፒዮንስ ሊግ ያደርጋል ። 
ፒ.ኤስ.ጂ በምድቡ ከናፖሊ እና ሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች የተፈተነ ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፉ ጉዳይም አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ። 
ኔይማር በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች ለፒ.ኤስ.ጂ 16 ጊዜ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን 10 ግብ አስቆጥሮ 5 ኳስ ለጎል አመቻችቶ አቀብሏል ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...